ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲወሰዱ የነበሩ ምልምል ታዳጊ ልጆች በፋኖ ነፃ!
ሕፃናትን ለጦርነት ማዋል አለማቀፋዊ ወንጀል ነው። ይህን በመተላለፍ የብልፅግና አረመኔ አመራር በተደጋጋሚ ህፃናትን ከትምህርት ቤት እየመለመለ ወደ ስልጠና እየላከ በጦርነት እያስጨፍጭፍቸው ይገኛል። በውጊያ የማረክናቸው ሕፃናትም የስነልቦና ጫና ውስጥ በመግባታቸው የጤና መታወክና የአዕምሮ ሰላም እንዳጡ በተለያዩ ጊዜ ያረጋግጠው ጉዳይ ነው።
ይህን የመከላከል ሀላፊነት የወደቀበት የአማራ ፍኖ በተለያዩ ጊዜ ስልጠና እንዳይገቡ በደፈጣ ከነመኪና በመማረክ የስነልቦና ስልጠና እና የተሀድሶ ስልጠና እየሰጠ ወደ ቤተሰቦቻቸው መላኩን ተያይዞታል። ከዚህ በፊትም ደብረማርቆስ ዙሪያ በበረኸኛው ጅበላ ብርጌድ በርካታ ህፃናትን በ2016ዓ.ም ማስለቀቁ የሚታወስ ነው።
ዛሬም ታፍነው ወደ ማሰልጠኛ ቦታ ሲሄዱ የነበሩ የአማራ ህጻናት በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦር ቃኝና መሀንዲስ ሻለቃ ከመንገድ ላይ በመማረክ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
©አፋብኃ| ቴወድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ