የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የማኅበረ ቅዱሳን አባል በታጣቂዎች ተገደሉ

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የማኅበረ ቅዱሳን አባል በታጣቂዎች ተገደሉ 
የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥር በምትገኘው በሐረቶ ማርያም በዓሉን አክብረው ሲመለሱ ሻንቡ ከተማ መዳረሻ ሲደርሱ የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዹጉማ እና በርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞችና ወጣት የማኅበራት አገልጋዮች በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መወሰዳቸው ይታወቃል።
ሌሎቹ ተፈትተው ቆይተው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዹጉማ ኡፋ እና የማኅበረ ቅዱሳን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች መገደላቸው ተገልጿል።
==== ነፍስ ይማር አባቶቻችን። እግዚአብሔር አምላክ ቤተሰቦቻችሁን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን እንዲሁም መላውን ሕዝበ ክርስቲያን ያጽናናልን።
(ምንጭ @የኢኦተ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን)Image