ኤርትራ ከኢጋድ በድጋሚ መውጣቷን ዛሬ አስታወቀች

ድርጅቱ ግዴታዎቹን ባለመወጣቱ ሕጋዊነቱ እየተሸረሸረ በመሄዱ እንደሆነ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኤርትራ፣ ኢጋድ በቀጠናው መረጋጋት ለማስፈን አስተዋጽኦ ማድረግ አልቻለም በማለትም ተችታለች።

ኤርትራ ከ18 ዓመታት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ከኢጋድ ወጥታ የነበረ ሲሆን፣ ሆኖም ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ከሰባት ዓመታት በፊት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ድርጅቱን በድጋሚ ተቀላቅላ ነበር።