በኢትዮጵያና በሕዝቦቿ የሚመጣ ማንኛውም ጠላት ጠላታችን ነው – የአማራ ፋኖዎች


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070
May be an image of 9 people, people standing and outdoorsመንግሥት ለሕዝቡ ያደረገውን ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ ከጎንደር ከተማ የተነሱት የአማራ ፋኖዎች ደባርቅ ከተማ ሲደርሱ ሕዝቡ የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል፡፡ የጎንደር ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ ሰለሞን አጠናው “አሸባሪው ትህነግ ለ27 ዓመታት የአማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲበድል ኖሮ በኋላም መከላከያ ሠራዊት ላይ ክህደት ፈጽሟል ነው ያለው፡፡ በዚህ ወቅትም ፋኖው ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ጋር በመሆን በትህነግ ላይ ተጋድሎ መፈጸሙን ተናግሯል፡፡
ፋኖ ሰለሞን “አፈር ልሶ የተነሳው ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ አሁንም ጥቃት ፈጽሟል፤ ይህን አሸባሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ቆርጠን ተነስተናል” ብሏል፡፡ይህን ለማድረግም ፋኖው ዝግጁ መሆኑን አስረድቷል። አሸባሪው ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ ጭቆና ብቻ ሳይሆን በሐሰት ትርክት አማራ እንዲጠላ ለ27 ዓመታት ሢሠራ ቆይቷል ያለው ደግሞ ፋኖ ዮሐንስ ንጉሡ ነው፡፡
May be an image of 3 people, people standing and outdoorsየአማራ ፋኖ ዓላማ ከአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ጋር በመቀናጀት ለአማራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስጋት የሚሆንን ቡድን በመታገል የሕዝብን ደኅንነት ማረጋገጥ ነው ብሏል። ፋኖ ዮሐንስ ዛሬም አሸባሪው ትህነግ በአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃት ከፍቷል፤ በዚህም የአማራ ሕዝብ ህልውና አደጋ ላይ በመውደቁ የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለናል ነው ያለው፡፡ ከጽጥታ ኀይሉ ጋር በመቀናጀትም አሸባሪው ቡድን ላይ የማያዳግም ርምጃ እንወስዳለን ብሏል፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊና የከተማው የሎጅስቲክስ አስተባባሪ ቻላቸው ካሴ የአማራ ፋኖ እስካሁን ከአሸባሪው ቡድን ጋር በተደረጉ ጦርነቶችም ሆነ በየአካባቢው በሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮች ጠላትን በመዋጋት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አሁንም የመንግሥትን ጥሪ ተቀብሎ አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ በሙሉ ዝግጁነት በመነሳቱ ሕዝቡና ከተማ አስተዳደሩ ደማቅ አቀባበል በማድረግ ድጋፉን ገልጿል ብለዋል።
የአማራ ፋኖዎች ከጎንደር ከተማ ጀምሮ በአምባጊዮርጊስ፣ በገደብዬ፣ በዳባት፣ በወቅን፣ በደባርቅ ከተማና በአካባቢው ሕዝብ የተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልና አሸኛኘት ከፍተኛ ወኔ ፈጥሮልናል ነው ያሉት፡፡ ከመንግሥት የጦር ኃይል ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውንም አቀባበል ላደረገላቸው ሕዝብ ገልጸዋል፡፡
May be an image of one or more people, people standing, outdoors and crowd