Blog Archives
አፍራሽ ይዞታ ያላቸው የባለሥልጣናት_ንግግሮች_ሊገሩ_ይገባል!
(በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ እናት ፓርቲ እና ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ)
ከባለሥልጣናት አንደበት የሚወጡ የማይጠበቁ ቃላት አንድ ጊዜ ሲሆን የአፍ ወለምታ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል። በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተለያዩ ጊዜያት የሚነገሩ ተመሳሳይ ንግግሮች ሥርዓታዊ የአመለካከት አቅጣጫን የሚያመላክቱ መሆናቸው ግን ጥርጥር የለውም። በዚህ ረገድ የሰሜኑ ጦርነት በሚካሄድበት ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሕወሓትና የትግራይ ክልልን አስመልክቶ “በሕዝብ አገር መሆን እንፈልጋለን ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ካሉ እኮ ራሳቸው የቀረጹት ሕገ መንግሥት ላይ የተቀመጠ እኮ አንቀጽ አለ። በዚያ መሠረት መሄድ ነው!” ብለው መናገራቸው የአንድ ወቅት መነጋገሪያ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም በቅርቡ ባደረጉት ንግግር “ለመገንጠል ደግሞ ጉልበት አያስፈልግም። አሠራር ሕገ መንግስት አለ። በዚያ ሂዱ።” ሲሉ ተደምጠዋል።
እነዚኽ በይፋ የተነገሩትን ለአብነት ጠቀስን እንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲኽ ለብልጽግና ሹማምንት ቅርበት የነበራቸው ግለሰቦች እያወጧቸው ያሉና ማስተባበያም ማስተማመኛም ያልተሰጠባቸው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ንግግሮች ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ናቸው። የኾነው ኾኖ በይፋም ከመጋረጃ ጀርባም የተነገሩና የተባሉ አደገኛ ንግግሮች በስሕተት የተነገሩ እንዳልኾኑ ከድግግሞሹና ከተናገሩት ባልሥልጣናት ደረጃ ማየት የሚቻል ሲኾን ይኽም ሥርዓታዊ አቋም ነው ወይ?! ለማለት ያስገድዳል፡፡
በሌላ በኩል በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አገር የምትገኝበት መጠነ ሰፊ የርስ በርስ ጦርነት አልበቃ ብሎ ባለፈው ያደናቀፈንና ሚሊዮን ዜጎቻችንን ጭዳ ያደረገው የጦርነት እንቅፋት ዳግም ሊመታን ከቋፍ መድረሱን እያየን ነው፤ ከላይ የተጠቀሱ ንግግሮችም
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ኹኔታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማከናወን “ተስፋ ሰጪ ነገሮች የማይታዩበት” ነው ሲል የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓረቲዎቸ ስብስብ – ኮክሰ ሥጋቱን ገለፀ። በቅድሚያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “የአሰራርና ተቋማዊ” ያላቸው ችግሮች እንዲፈቱ የጠየቀው ኮከስ በተቋሙ “እውነተኛ ሪፎርም ከሌለ ተዓማኒ፣ አካታች፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሊኖር አይቸልም” ብሏል። በዋናነት 8 የፓለቲካ ድርጅቶች ንቁ ተሳትፎ ያደርጉበታል የተባለው ኮከስ ስለ ምርጫ ከመታሰቡ በፊት በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ጦርነት እና ግጭቶች እንዲቆሙ፣ ሰላም እንዲሰፍን እና በተለይ ከኤርትራ ጋር እየተስተዋለ ያለው ውጥረት እንዲፈታ ጠይቋል።
የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓረቲዎቸ ስብስብ – ኮክሰ ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ግጭጦች እንዲቆሙ ደጋግሞ ቢጠይቅም አሁንም ለሀገር ደኅንነት ሥጋት ሆነው መቀጠላቸውን ገልጿል። የዚህ ስብስብ አባል ፓርቲ የሆነው የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል ሞጊሶ “ጦርነት ይብቃ” የሚለው አሁንም ዋና የጥሪያቸው ጭብጥ መሆኑን ገልፀዋል።
“ዘላቂ ሠላም እንዲመጣ ከተፈለገ ጦርነት መቆም አለበት። ይሄ ነገር እየሰፋ በሄደ ቁጥር ይቺ ሀገር እያየን ልትፈርስ ትችላለች”።
ኮከስ ቀጣዩን ምርጫ ለማከናወን አስቻይ ኹኔታ የለም ብሏል
ኮከስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከጅምሩ “የነጻነት እና የገለልተኝነት” ጥያቄዎች እንደሚነሱበት በመጥቀስ አሁንም አሉበት ያላቸው “የአሰራርና ተቋማዊ ችግሮች” እስካልተፈቱ ድረስ “ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ ሊኖር አይችልም” ብሏል፡፡ “እውነተኛ ሪፎርም ከሌለ ተዓማኒ፣ አካታች፣ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ” ሊኖር እንደማይችልም አቋሙን ይፋ አድርጓል።
“ሕዝብ ሰላማዊ ባልሆነበት ኹኔታ ዲሞክራሲን አይደለም የሚመርጠው። ሕዝብ
በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ የሚገኙ 14 ወረዳዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና እና ቦረና ዞኖች ሕዝባዊ ተቃዉሞ መቀስቀሱን ዋዜማ ሰምታለች።
ይህ ውሳኔ የተወሰነው የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባኤው ላይ መሆኑን ያስረዱት ምንጮች፣ ይህንኑ ተከትሎ በቅርቡ እንደ አዲስ በተዋቀረው የምስራቅ ቦረና ዞን መቀመጫ ነጌሌ ቦረና ከተማ እና የቦረና ዞን መቀመጫ በሆነችው ያቤሎ ከተማ፣ እንዲሁም በሌሎች ወረዳዎች ከዛሬ ማለዳ አንስቶ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ መሆኑን ዋዜማ የደረሳት መረጃ ያመልክታል።
ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ በምክር ቤቱ የተወሰኑት 14ቱ ወረዳዎች በሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሚገኙት ቦረና፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እንዲሁም ከድሬደዋ አካባቢዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ውሳኔ የተሰጠባቸው እንደሆኑ ምንጮች ነግረውናል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 21፣ 2017 ዓ፣ም እኩለ ቀን ድረስ በፌዴራልም ሆነ በኦሮሚያ ክልል መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ የተባለ ነገር የለም። [ዋዜማ]
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ለግብፅ የ4.7 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ሽያጭን አፅድቋል።
በመሳሪያ ሽያጩ መሰረት ግብፅ ራዳር፣ ሚሳኤሎች እና የሎጅስቲክስ እንደዚሁም የኢንጂነሪንግ ድጋፎችን ከአሜሪካ ታገኛለች።
አሜሪካ ለግብፅ የምትሰጠው የአየር ስርዓት መሳሪያ ሂሊኮፕተሮችን፣ ድሮኖችን እንደዚሁም ክሩዝ ሚሳኤሎችን ለመመከት ያስችላል።
አሜሪካ ይህንን ሽያጭ የኔቶ አባል ሃገር ካልሆኑት ዋነኛ አጋሮቿ ውስጥ የሆነችው የግብፅን ደህንነት ለማሻሻል መሆኑን ገልፃ ይህም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ያስችላል ብሏል።
በተጨማሪ ለግብፅ ጦር ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ 26 የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞች እና 34 ኮንትራክተሮች ወደ ግብፅ ያመራሉ ተብሏል።
የመሳሪያ ሽያጩን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ያፀደቀው ሲሆን በቀጣይ የኮንግረሱ ውሳኔ ይቀረዋል።
ከ1979 ጀምሮ ግብፅ ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረሟ ከአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ እና ድጋፍ በገፍ እያገኘች እንደሆነች ይታወቃል።
ግብፅ በተመሳሳይ በ2024 የ5 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ግዢን ከአሜሪካ ፈፅማለች።
ሃገረ ግብፅ ከእስራኤል በመቀጠል ከአሜሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የወታደራዊ ድጋፍ የሚደረግላት ሃገር ስትሆን ከ1979 ጀምሮ በየአመቱ የ1.3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ከአሜሪካ ታገኛለች።
Source: Al Jazeera, Madamasr, Defensepost
መቀጣጫው ለእኔ ሳይሆን ለእናንተ ነው! ( ልደቱ አያሌው )በቅርቡ- “መኖሪያ ቤትህን በ10 ቀን ውስጥ የማህበረሰብ ፖሊስ ጣቢያ ላደርገው ነው” ብሎ የዛተው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አገዛዝ ዛቻውን ለመፈጸም 10 ቀንም መታገስ አልቻለም። ከሁለት ቀን በፊት ያለምንም የፍርድ ቤት ውሳኔ የቤተሰቤ ንብረት የሆነውን መኖሪያ ቤቴን ከነ ሙሉ እቃው በመቀማት (መውረስ አይደለም) ፖሊሶች ገብተውበታል። ቀደም ሲል እንዳሉት የማህበረሰብ ፖሊስ ጣቢያ ያድርጉትወይም የባለስልጣን መኖሪያ እስካሁን በግልፅ አላዎቅነም። ይህንን ማድረግ አልበቃቸው ብሎም የቤቴን ጠባቂያለምንም ምክኒያት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው አስረውታል።ይህ አገዛዝ አይፈጽመውም ብዬ የምገምተው ምንም ዓይነት ነውርና ወንጀል ባይኖርም፣ ይህ የጠቅላይሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ዐይን ያዎጣ የወንጀል ድርጊት የፖለቲካ አንደምታው ምን እንደሆነ እይታየንለህዝብ ማካፈል ስለፈለግሁ ይህችን አጭር መጣጥፍ ላስነብባችሁ ወደድኩ።በኢትዮዽያ ፖለቲካ ተሳታፊ ከሆንኩ 33 ዓመት ሆኖኛል። በ27 ዓመቱ የኢህአዴግ አገዛዝ 5 ጊዜ ታስሬ ተፈትቻለሁ። ለ18 ቀናት የቤትና የቢሮ ውስጥ እገታ፣ ለ120 ተከታታይ ቀናት የደህንነት ክትትልና ማዋከብ፣ቢያንስ ለ20 ተከታታይ ዓመታት የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶብኛል። አጸያፊ ስድብና መለስተኛ ድብደባ የደረሰብኝ ወቅትም ነበር። በእነዚህ ሁሉ ተጽዕኖዎች ምክኒያት ለተለያዩ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚና የጤና ችግሮች ተጋላጭ ሆኛለሁ።ይህ ሁሉ በደል ሲደርስብኝ ግን በወቅቱ በስልጣን ላይ የነበረው የኢህአዴግ አገዛዝ በእኔ ላይ ለሚፈጽማቸውህገ-ወጥ ድርጊቶች ቢያንስ ህጋዊ ሽፋን ለመስጠትና ለማስመሰል በተቻለው አቅም ይሞክር ነበር። በእኔየፖለቲካ ተሳትፎ ምክኒያትም በቤተሰቦቸና በጓደኞቸ ላይ አንድም ጊዜ ችግር ለመፍጠርና የግል ንብረቴን ለመውረስ ሞክሮ አያውቅም። አባል የነበርኩበትን ፓርቲም ለመከፋፈልና ለማዳከም እንጂ

በደምቢዶሎ ከተማ በሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ተመርቃ መንገድ ላይ አትክልት እና ፍራፍሬ በመቸርቸር የምትተዳደረው መምህርት ፎቶ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተጋርቶ በርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል።
አባይነሽ ሐምቢሳ የተባለችው ይህች መምህርት ከደምቢደሎ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ የትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪዋን ያገኘችው በማዕረግ ነው።
ይህች መምህርት ላለፉት ዓመታት ትምህርት በሚዘጋበት በክረምት ወቅት እንዲሁም በእረፍት ቀኗ ቅዳሜዎችን መንገድ ላይ በመቸርቸር ነው ኑሮዋን የምትደግፈው።
ለ13 ዓመታት በመምህርነት ያገለገለችው አባይነሽ በየወሩ የምታገኛት 7,500 ብር ደመወዝ ካለው የዋጋ ግሽበት ጋር ተያይዞ ኑሮዋን መደጎም ስላዳገታት ነው ወደ ጉሊት የወጣችው።
“የማገኘው ደሞዝ ልጆቼን ለማስተዳደር፣ ማኅበራዊ ሕይወቴን ለመደገፍ፣ ለትምህርት፤ ለአጠቃላይ ለኑሮዬ በቂ አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ለመንግሥት ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ በቂ አይደለም፤ ያለውን የኑሮ ውድነትን ያገናዘበ አይደለም” ትላለች።
ከማስተማር ሥራዋ ጎን ለጎን ትምህርቷን በከፍተኛ ደረጃ መቀጠሉ አስፈላጊ ሆና ያገኘችው አባይነሽ፣ የማስተርስ ትምህርቷን ለመደጎምም ሌላኛው አማራጩ ጉሊት ነበር።
“በወር ደሞዜ የትምህርቴን ከፍዬ፣ ኑሮዬን ደግፌ፣ ለልጆቼ አውጥቼ አይሆንም” ስትል የአራት ልጆች እናት የሆነችው አባይነሽ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጻለች።
በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ዩብዶ ወረዳ የተወለደችው አባይነሽ የጉሊት ችርቻሮዋን የጀመረችው ከሁለት ዓመታት በፊት ነው።
ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ እና አቮካዶ የመሳሰሉ ፍራፍሬዎችን ከደምቢዶሎ ከ20 አስከ 25 ደቂቃ በእግር የሚያስኬድ መንገድ ከሚጠይቀው ስፍራ ተሸክማ አምጥታ በከተማዋ ትችረችራለች።
ገበያ በደራበትም ቀንም ከ200 አስከ 500 ብር ታገኛለች።
“ከማገኘው ትርፍ 100 ወይም 200 ብር አስቀምጬ ቀሪውን ደግሞ ለቤተሰቤ የሚያስፈልጉ እንደ ሳሙና፣ ስኳር ወይም
በአዲስ አበባ ከተማ ከትናንት ጀምሮ ተመልሶ የመጣው መጠነ-ሰፊ የወጣቶች አፈሳ
“ሲቪል ፖሊስ በየመንገዱ እወስድሀለው እያለ ይደራደራል፣ ሌብነቱ ሀላል ወጥቷል። በየቀኑ ከመዝናኛ ቦታ እየወሰዱ በብር ተደራድረው ይለቋቸዋል።”
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://tinyurl.com/6mcu6xfd
የእነ አቶ ዮሐንስ ቧያሌው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ የምስክር አሰማም ሂደት ለጊዜው ታግዶ እንዲቆይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጠ
የተከሳሽ ጠበቆች በይግባኙ አቤቱታ ላይ እንደገለፁት አቃቤ ሕግ 15 ምስክሮችን ካሰማ በኋላ ቀድሞ በስም ዝርዝሩ ውስጥ ያልተካተተን ምስክር በመጋረጃ ጀርባ እንዲመሰክር ብሎ ማቅረቡ የተከሳሾችን መብት በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ይሄው የስር ፍርድ ቤቱ ብይን ሊነሳ ይገባል የሚል ነው።
ተጨማሪ ያንብቡ:
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/65f?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
የጠላት 78ኛ ክ/ጦር ተደመሰሰች።
በአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ እዝ 4ተኛ ደጅ አዝማች ኮር የጎቤ ክፍለ ጦር ዛሬ ሐምሌ 15/2017 ዓ.ም
በቁጥር አንድ እና በኪኒቸሩ መካከል ባደረገው ውጊያ የተገኘ ከፊል ምርኮ:-
1.አስር/10 ተሺከርካሪ
2.አንድ ሞርታር ከ6 ቅንቡላ ጋር
3.አንድ ዲሽቃ ከ18 ሳጥን /አስቃጥላ ተተኳሺ ጋር
4.ከ 117 በላይ ነፍስ ወከፍ
5.ቁጥሩ ያልታወቀ ብሬን እና ስናይፐር
6.ብዙ የክላሺ እና ብሬን ተተኳሺ
7.ቁጥሩ ያልታወቀ ምርኮኛ
👉የጠላት ኃይል 78ኛ ክፍለ ጦር(የቅጥረኛው ግርማ ኃይል ነው )
💉2 ሬጅመንት የጠላት ኃይል ተደምስሷል::
💉ሻለቃ አስረስ የተባለው የጠላት ጦር መሪም ተገሏል::
👉ኦፕሬሺኑን በበላይነት የመሩት የጎቤ ክፍለ ጦር አመራሮች
1ኛ. አርበኛ ኢሳያስ ሰጠኝ=ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
2ኛ. አርበኛ መንገሻ አስራት=ም/ዋ/አዛዥ
3ኛ.አርበኛ እሸቱ ምስጋናው=ኦርዲናንስ ኃላፊ
4ኛ.አርበኛ እርታው ታገለ=ሕዝብ አደረጃጀት ኃላፊ ናቸው::
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (UNESCO) ልትወጣ ነው።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዳግም ወደ ነጩ ቤተመንግስት ከተመለሱ በኋላ አሜሪካ ከአለም አቀፍ ተቋማት እንድትወጣ እየሰሩ ሲሆን አሁን ከዩኔስኮ እንድትወጣ መወሰናቸውን የነጩ ቤተመንግሥት ምክትል ቃለ አቀባይ አና ኬሊ ተናግረዋል።
አና ኬሊ የዩኔስኮ የባህል እና ማህበራዊ ፖሊሲ አሜሪካውያን ድምፃቸውን ከሰጡበት ፖሊሲ ጋር ስለሚቃረን ፕሬዚደንቱ አሜሪካ እንድትወጣ መወሰናቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ቃለ አቀባይ ታሚ ብሩስ የአሜሪካ በዩኔስኮ መቀጠል ከብሔራዊ ጥቅሟ በተቃራኒ መሆኑን ገልፀዋል።
ታሚ ብሩስ ተቋሙ ውስጥ ፀረ ሴማዊነት አለ ያሉ ሲሆን ተቋሙ ፍልስጤምን እንደ አባል ሃገር መቀበሉ ከአሜሪካ ጥቅም በተቃራኒ ነው ብለዋል።
የዩኔስኮ ዳይሬክተር ኦድሪ አዙላይ ተቋማቸውን ይህንን ውሳኔ ሲጠብቅ እንደነበር ገልፀው ሲዘጋጁበት እንደነበርም ገልፀዋል።
አሜሪካ ከተመድ የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ተቋምም በፈረንጆቹ ታህሳስ 31፥2026 ትወጣለች ተብሏል።
አሜሪካ በ1945 ዩኔስኮን ከመሰረቱ ሃገራት አንዷ ስትሆን በ1984 ከፋይናንስ አያያዝ እና ከአሜሪካ በተቃራኒ ቆሟል በሚል ከወጣች በኋላ ተቋሙን በ2003 ዳግም ተቀላቅላለች።
በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ፕሬዚዳንት ሆነው በተመረጡ ጊዜ አሜሪካን ከተቋሙ አስወጥተው የነበረ ቢሆንም ጆ ባይደን ዳግም መልሰዋት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ሁነት መሆኑ ይታወሳል።
Source: CNN
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና
በላይ ዘለቀ ዕዝ
ጀግናው ሰራዊታችን ሀምሌ 11/2017 ዓ.ም የአገዛዙን ሰራዊት የሚደመስስ የረቀቀ ወታደራዊ ዕቅድ በማቀድ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ በመተማ ወረዳ ሽመለ ጋራ፣ደለሎ ቁጥር አንድና ቁጥር አምስት በከፈተው ወታደራዊ ማጥቃት ከ170 በላይ የተደመሰሰ፣ከ40 ጠላት እጅ ሰቶ ተማርኳል፣ከ100 በላይ የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ሲማረክ 06 የቡድን የጦር መሳሪያ ብሬንና ስናይፐር ተማረኳል።
አንድ ዲሽቃ ሞተራይዝድ የተማረከ ሲሆን 05 አይኮም ወታደራዊ ሬድዮን ጨምሮ 01 ሽጉጥ የተማረከበት ስኬታማው ኦፕሬሽን ነው።
ዘግይቶ በደረሰን መረጃ መሰረት ደጃዝማች 4ኛ ኮርና ከመይሳው ካሳ 2ኛ ኮር አጣናው ዋሴ ክ/ጦር በቅንጅት የብርሃኑ ጁላ ታጣቂን በበርሃማው ጠረፋማ ቀጠና አንጀቱን በጎተቱበት ውጊያ የጠላት 78ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ 2ኛ ሬጅመንትም በከፊል ተደምስሳለች።
የዓብይ አህመድ 78ኛ ክ/ጦር 1ኛ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ኤፍሬምም በደለሎ ቁጥር አንድ ከተደመሰሱት መካከል እንደሚገኝበት ማረጋገጥ ተችሏል።
ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!
አፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ
ዮሐንስ ንጉሱ ሙጨ
Amhara Fano National Force
@AmharaFanoNF
·
39m
የኤርትራው ፕሬዝደንት የብልፅግና ፓርቲን ‘ርካሽ ውሸት’ በማሰራጨት እና ለጦርነት ዝግጅት በማድረግ ከሰሱ
ከኢትዮጵያ የባህር በር አጀንዳ ጀርባ የኤምሬቶች ወደብ የማስፋት ፍላጎት አለ በማለት የኤርትራው ፕሬዝደንት ሲናገሩ ተደመጡ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣብያ ጋር ረዘም ያለ ቃለ-መጠይቅ አድርገው ነበር። በቃለ-መጠይቃቸው አብዛኛውን ከኢትዮጵያ ጋር እየተካረረ ስለመጣው ግንኙነት እና የግጭት ስጋት አንስተዋል።
“በግልፅ ሲታይ እነዚህ የብልፅግና ፓርቲ አጀንዳዎች ሳይሆኑ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፕሬዝደንት [መሐመድ ቢን ዛይድ] በቀጠናው ወደቦችን አስፋፍቶ የመያዝ አጀንዳ አካል ነው።” https://shabait.com/2025/07/19/highlights-of-president-isaias-afwerkis-interview-with-local-media-outlets-2/
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ አወዛጋቢውንና የተሻሻለውን የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ ለውጥ ሳይደረግበት በ5 ተቃውሞና በ12 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል። ግብር የሚቆረጥበት ዝቅተኛ ደመወዝ ከ2 ሺሕ ብር ወደ 8 ሺሕ 324 ብር ከፍ እንዲደረግ የቀረበው ሃሳብም ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል። አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት፣ ማሻሻያው የመንግሥት ሠራተኞችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ አላደረገም በማለት ተችተው ነበር። የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ፣ የመንግስት ሠራተኞችን ኑሮ ለማሻሻል፣ የመኖሪያ ቤት ጥናት እየተደረገ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የተሻሻለውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ዛሬ በሁለት ተቃውሞና በአራት ድምጸ ተዓቅቦ አጽድቋል። በምርጫ ጣቢያ ደረጃ የነበረው የቅሬታ ሠሚ ኮሚቴ ለምን እንደቀረ አንድ የምክር ቤት አባል የጠየቁ ሲሆን፣ የዲሞክራሲና ፍትሕ ቋሚ ኮሚቴም በክልል ደረጃ ብቻ ቅሬታ ሠሚ ኮሚቴ ማዋቀሩ የተሻለ ኾኖ ስለተገኘ እንደኾነ አስረድቷል።
አዲስ አገር ዓቀፍ ፓርቲዎች በአራት ክልሎች የድርጅት መስራች አባል ማፍራት እንዳለባቸው የሚለው ድንጋጌም፣ ስድስት ክልሎች እንዲኾን ተደርጓል።
“አዲሱ የደመወዝ ገቢ ግብር ረቂቅ የኑሮ ጫናን ያገናዝብ” የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን
በትናንትናው እለት ለኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በርካቶችን አከራክሯል፡፡
በምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዘጋጅነት የቀረበው ረቂቁ ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ መነሻ ከዚህ በፊት ከነበረው 600 ብር ወደ 2000 ብር ከፍ እንዲል ሃሳብ ያቀረበ ቢሆንም በበርካቶች እይታ ግን አመርቂ አለሆነም፡፡
በተለይም ከዚህ በፊት ግብር የሚቆረጥበት የደመወዝ ክፍያ መጠን መነሾ በትንሹ 8 ሺህ 300 ብር ገደማ መሆን አለበት በሚል ምክረሃሳብ አቅርቦ የነበረው የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን ትናንት የቀረበውን ረቂቅ ከመጽደቁ በፊት ዳግም እንዲታይ አሳስቧል፡፡
የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?
ስሜ ይቆይ ብለው አስተያየታቸውን ያጋሩን አንድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚያስተምሩ መምህር የኑሮ ጫና ለሰራተኛው የሚከፈለውን ደመወዝ ጥሎት በመሄዱ በብዙ መልኩ እልባት ይሻል ይላሉ፡፡ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመከረበት አዲሱ የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ የኑሮና የታክስ ጫና ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ እና ከታክስ ስርአት ጋር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት አበክሮ የሚያገናዝም መሆን አለበት የሚሉ ድምጾች ክፍ ብለው ተሰምተውበታል፡፡ ታዲያ በዚሁ ላይ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ ያቀረቡት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መምህሩ፤ አሁን ያለው የኑሮ ጫና እንኳን ከፍተኛ ቀረጥ (ታክስ) ኑሮበት በምንም የማይያዝ እየሆነ ነው ይላሉ፡፡ “ገቢያችን ከኑሮ ውድነቱ አኳያ በጣም ወደ ኋላ ቀርቷል” ያሉን አስተያየት ሰጪው “አሁን የሚከፈለውን የሰራተኛው ደመወዝ
በአፋር ክልል ካሉ ታጣቂዎች ወደ ትግራይ ክልል ማንኛውም ትንኮሳ የሚመጣ ከሆነ ተጠያቂው የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ነው ሲሉ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ ገለፁ። በአፋር ካሉ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች ታጣቂዎች ጋር ያለው ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ያሉት ፕሬዝደንቱ፥ ይሁንና የውክልና ግጭት ለመፍጠር ከተሞከረ ግን ጉዳዮ ከፌደራል መንግስት ጋር ነው የሚሆነው ሲሉ ጀነራል ታደሰ ወረደ አስታውቀዋል። ህወሓትም በበኩሉ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አውጥቶት በነበረ መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ታጣቂዎች እያሰባሰበ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጥሪ
ትላንት በመቐለ ሓወልቲ ሰማእታት አደራሽ በነበረ የትግራይ ሰማእታት መታሰብያ መዝግያ ስነስርዓት ንግግር ያሰሙት የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ በክልሉ ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል። ከህወሓት ክፍፍል በኃላ የተለየ ፖለቲካዊ አቋም በመያዝ ከነባር የትግራይ ሐይሎች በመለየት በአፋር ክልል እየተደራጁ የቆዩት ታጣቂዎች ጉዳይ በዝርዝር ያነሱት ጀነራል ታደሰ ወረደ፥ ከእነዚህ ታጣቂዎች በኩል የሚደረግ ማነኛውም ትንኮሳ ግዚያዊ አስተዳደሩ ጉዳዩ የእነሱ አድርጎ ሳይሆን የፌደራሉ መንግስት ትንኮሳ አድርጎ እንደሚያየው ገልፀዋል።
በትግራይ የግብርና ምርት በግብአቶች እጥረት ተመናምኗል ተባለ
ጀነራል ታደሰ “በእዛ አቅጣጫ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ትንኮሳ እንደ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ጉዳዮ እዛ ያሉት [ታጣቂዎች] አድርጎ አይወስደውም። ወይም የፌደራል መንግስት ነው፣ አልያም የአፋር ነው። እዛ ካሉት [ታጣቂዎች] ጋር ያለው ነገር በሰላም መፈታት አለበት። የሆነ ይሁን ትንኮሳ ግን ከአፋር አቅጣጫ ከመጣ
የፌዴራል ገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ተግባራዊ ከተደረገ የአገሪቱን የውጭ ኢንቨስትመንት ሊጎዳ እንደሚችል ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አሳሰበ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ የጀትና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌዴራል የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. በጠራው የምክክር መድረክ የንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች፣ የሒሳብ ባለሙያዎች፣ የፌዴራልና ክልል መንግሥታት ተወካዮች፣ የሙያ ማኅበራት፣ የንግድ ተቋማትና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ነው ማሳሰቢያው የተሰጠው፡፡
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በውይይት መድረኩ ከተገኙ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን፣ ድርጅቱን ወክለው የተገኙት አቶ ዳዊት ፍሰሐ በረቂቅ ሕጉ ላይ ቢስተካከሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል፡፡
አንድ ድርጅት እየከሰረ መቀጠል እንደማይችልና ኪሳራው ከቀጠለ እንደሚዘጋ በረቂቅ ሕጉ ላይ መጠቀሱን ገልጸው፣ ነገር ግን እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላለ ልዩ የኢንቨስትመንት ባህሪ ላለው ተቋም የማይሠራ በመሆኑ ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል፡፡
‹‹ያለን የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለ15 ዓመታት የሚል ነው፡፡ ይህ ፈቃድ በየ15 ዓመት እንደሚታደስ ሆኖ ለ30 ዓመት የሚቆይ ነው ብለን ነው የምናስበው፡፡ ኢንቨስትመንታችን በሙሉ ለ30 ዓመታት መቆየትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ ናቸው፡፡ ኢንቨስትመንታችን ትርፍ አለ ብለን በምናስብባቸው ቦታዎች ሁሉ አይደሉም፡፡ በየቦታው ታወሮችን መገንባትን ጨምሮ ብዙ ካፒታል የሚያስወጡ ሥራዎች አሉብን፡፡ የኔትወርክ ሽፋን ለማስፋት የመገንባት ግዴታዎች አሉብን፡፡ በአራት ዓመታት ውስጥ ለመሠረተ ልማት ማስፋፊያና ግንባታ ከ350 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ አድርገናል፡፡ ይህን የምናደርገው በረዥም ጊዜ ትርፍ ይመጣል በሚል ዕቅድ ነው፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ዳዊት አክለውም፣ ‹‹ኢንቨስት የምናደርገው ትርፍ በሚገኝባቸው ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ይህ ባለበት ሁኔታ
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክተው ስላደረጉት ንግግርም ሆነ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠርተው ስለነበራቸው ውይይት ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጠቡ፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታው ሀደራ አበራ (አምባሳደር)፣ ከአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋ ጋር ማክሰኞ ሐምሌ 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ውይይት ማድረጋቸውን ገልጾ ነበር፡፡
ውይይቱን በተመለከተም ሆነ የፕሬዚዳንት ትራምፕን ንግግር አስመልክቶ ሪፖርተር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመለከታቸውን ኃላፊዎች ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ያልተሳካ ሲሆን፣ በዋትስአፕ ጥያቄ የቀረበላቸው አምባሳደር ማሲንጋ ከሚኒስትር ደኤታው ጋር ስለነበራቸው ቆይታም ሆነ ስለትራምፕ ንግግር ለመናገር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን በመግለጽ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰኔ ወር ውስጥ ‹‹ትሩዝ›› በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው፣ በከፍተኛ መጠን ወደ ግብፅ የሚፈሰውን ውኃ ለሚገድበው ለግዙፉ የህዳሴ ግድብ አገራቸው ‹‹በሞኝነት›› የገንዘብ ድጋፍ ማድረጓን አስታውቀው፣ ነገር ግን በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ሰላም እንዲወርድ ጥረት ማድረጋቸውን በመጥቀስ፣ የሰላም ኖቤል ሽልማት ይገባቸው እንደነበር መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡
ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ትራምፕ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዋና ጸሐፊ ፒት ረትና ከተለያዩ ሹማምንቶቻቸው ጋር በዋይት ሐውስ ሲወያዩ፣ በዓለም ግዙፍ ከሆኑ ግድቦች አንዱ የሆነውና ‹‹ከግብፅ ወጣ ብሎ የሚገኘው›› ያሉትን የታላቁ የህዳሴ ግድብ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ትልቅ ችግር መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡ በዚህኛውም ንግግራቸው አገራቸው አሜሪካ ግድቡን ፋይናንስ ማድረጓን ጠቅሰው፣ የግድቡ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት ችግሩ ለምን እንዳልተፈታ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ትራምፕ የዓባይ
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ውስጥ የሚሰሩ ከ40 በላይ ሰራተኞች ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ተገኙ
“ሐሰተኛ ማስረጃ ይዘው ከተገኙት ውስጥ እንደ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴዎች ባለሙያዎች እና ዳይሬክተሮች ይገኙበታል”
የመሠረት ሚድያ የፕሪሚየም አባል ከሆኑ በፅሁፍ የተዘጋጀውን ይህን መረጃ ይከታተሉ ⤵️
https://open.substack.com/pub/meseretmedia/p/40?utm_source=share&utm_medium=android&r=bb7g
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ የኢትዮጵያውን ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በገንዘብ ደግፋለች ሲሉ ርግጠኝነት በሌለው መልኩ ትናንት በድጋሚ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ ግድቡ ወደ ናይል ወንዝ የሚሄደውን ውሃ ይዘጋዋል በማለትም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም፣ አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ እየሠሩበት መኾኑንና ችግሩ መፍትሄ እንደሚያገኝ በደፈናው ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ “መፍትሄ” ያሉት ምን እንደኾነ ግን አላብራሩም። መንግሥት፣ ከአንድ ወር በፊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ካኹን ቀደምም ይኹን ትናንት ለተናገሩት አወዛጋቢና አሳሳች አስተያየት፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ይፋዊ ምላሽ አልሰጠም።
የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፓርላማው ፍቃደኛ ከሆነ በስራ መውጫ ስዓት ፌስታል ይዘው ከሆቴል ተመላሸ ምግብ የሚለምኑ ሰራተኞች መኖራቸውን ማሳየት እንደሚችል ተናገረ፡፡
ኮንፌዴሬሽን ይህን ያለው በቅርብ ይጸድቃል ተብሎ በሚጠበቀው የፌዴራል ገቢ ግብር ማሻሽያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡
ከገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከሰራተኛው ለመቁረጥ የቀረበው ሃሳብ ውስብስብ የዋጋ ንረትን እና የድህነት መጠንን ያላገናዘብ ከመሆኑም በላይ ማጭበርበር ሳይኖር በአግባቡ ከደሞዙ ግብር የሚከፍለውን ሰራተኛ ከችግር የሚውጣ ሳይሆን ችግር ውስጥ የሚከት እንደሆነ የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዘዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ተናግረዋል፡፡

ሰራተኛው በቀን አንድ ጊዜ በልቶ መዋል አልቻለም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ወጪዎች ስላሉበት ነው ብለዋል፡፡
ተቀጣሪው ሰራተኛ ህክምና ሄዶ መታከም የማይችልበት ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ ያስረዱት አቶ ካሳሁን እውነት ለመናገር አንድ ሰው በ5 ሺ ብር ደሞዝ ቤት ኪራይ ይከፍላል ፣ ይበላል፣ ልብስ ይለብሳል ፣ ህክምና ይሄዳል ብለዋል፡፡
ህክምናውን እንተው እየጸለየ ይኑር ፤ቤት ኪራይውንም እንተወው በበረንዳ በሰዎች ላይ በጥገኝነት ይኑር ግን በቀን አንድ ጊዜ እየበላ መኖር የለበትም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
አንድ ድርጅት ከትርፉ 35 በመቶ ግብር ይከፍላል ያሉት የኢትዮጵያ የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ዋና ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ ሰራተኛውም 35 በመቶ ይከፍላል ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ሲሉ ጥያቄ
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ የዓመቱ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ሲመዘን
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ “በዲፕሎማሲው መስክ ውጤታማ የሥራ ስኬት ያስመዘገበችበት” እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ግንኙነትን ማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሥራ እንቅስቃሴማሳደግ፣ ከጎረቤት እና ሌሎች ሀገራት ጋር በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ትብብርን ማጉላት ውጤት ተመዝግቦባቸዋል የተባሉት መስኮች መሆናቸውንም ተቋሙ ይፋ አድርጓል።
ኢትዮጵያ ከምዕራባዊያን ሀገራት እና ተቋሞቻቸው ጋር ባላት ግንኙነት “ተቀባይነቷ የጨመረበት” ዓመት መሆኑን የጠቀሱ አንድ የዘርፉ ተንታኝ፣ የገንዘብ ተቋማት እያደረጉት ያለውን የብድር ድጋፍ አስረጂ አድርገዋል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት “አስጊነቱ አሁንም የቀጠለ” እና በጥቅሉ ሲመዘን “አድገናልም፣ ወድቀናልም የሚያስብል ኹኔታ ያልተፈጠረበት” ነው ብለዋል።
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል ዐቀባዩ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በኩል እንዳለው የተቋሙ የዚህ ዓመት የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ “ውጤታማ” ነበር። ቃል ዐቀባዩ ለዚህ ዝርዝር ጉዳዮችን የጠቀሱ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ ግን እነዚህ ናቸው። “የዲፕሎማሲ ግንኙነታችንን በማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅማችንን በማሳደግ፣ ከጎረቤት ሀገሮች እና ከተለያዩ ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ትብብር እንዲቀጥል፣ ቀጣናዊ ትስስርን፣ አሕጉራዊ እና አለማቀፋዊ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል”።የሰላም