Blog Archives

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበር አካባቢዎች ላይ ጥምር ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበር አካባቢዎች ላይ ጥምር ኃይል ለማሰማራት ተስማሙ ኢትዮጵያና ሱዳን በጋራ ድንበራቸው ላይ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጥምር ጦር ለማሰማራት ተስማምተዋል፡፡ የሁለቱ አገራት ጦር ኢታማዦር ሹሞች በትላንትናው ዕለት ካርቱም ላይ ተገናኝተው ከመከሩ በኃላ ነው ከስምምነት የደረሱት፡፡ የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ከማል አብዱል መዕሩፍ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በድንበር አካባቢ የሚሰፍረው የሁለቱ አገራት የጋራ ጥምር ጦር ሽብርን፣ ድንበር ዘለል የአማፂያን እንቅስቃሴን እና ህገ ወጥ ስደትን የመከላከል ተልዕኮ ይሰጠዋል፡፡ የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን በበኩላቸው በሁለቱ አገራት አወሳኝ ድንበር ላይ የሚሰፍረው የጋራ ጥምር ጦር የቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ በማድረግ ሂደት አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ ምንጭ፡አናዱሉ የዜና ወኪል
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በጎንደር ድንበር ጥሶ የሚገባው በሱዳን ጦር ብዙ ጥፋት እየደረሰ ነው።

የሱዳን ወረራ ጉዳይ! ትናንት ከቀኑ 9:30 ድንበር ጥሶ ገብቶ የነበረው የሱዳን ሰራዊት ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ ተመልሷል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ የሱዳን ጦር በገበሬው ላይ ሲተኩስ ባይደርስም ከሁለት ሰዓት በኋላ ወደ አካባቢው አቅንቶ ነበር። የአማራ ክልል ሚሊሻ ቀድሞ ወደ ቦታው መድረሱም ታውቋል። መከላከያ ሰራዊት እየደረሰ ያለው የሱዳን ጦር ድንበር ጥሶ፣ ገበሬዎችና ንብረታቸው ላይ ጉዳት ከደረሰ በኋላ ነው። ትናንት የአንድ ገበሬ ካምፕ በሱዳን ጦር ተቃጥሏል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሉአላዊነትን ባለማስከበሩ በሱዳን ጦር ብዙ ጥፋት እየደረሰ ነው። ለጥፋቱም ተጠያቂ የሚሆን አካል አልተገኘም። የዶክተር አብይ መንግስት በአማራ ገበሬዎች ላይ ለሚደርሰው ወረራና ስቃይ ቁብ አልሰጠም! በየጊዜው ወረራ ይፈፀማል። ሉአላዊነትና የዜጎችን ደሕንነት የማስጠበቅ ግዴታ ያለበት የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስት ግዴታውን እየተወጣ አይደለም።
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተላከላቸውን መልእክት ተቀበሉ።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር በድንበር አካባቢ የፀጥታ ችግር መከሰቱን ተከትሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ የተላከላቸውን መልእክት ተቀበሉ። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ሰሞኑን በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ተስተውሎ የነበረውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከላቸውን መልእክት ተቀብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት የላኩትን መልክእትም የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ናቸው ያደረሱት። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በዚሁ ወቅትም ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጋር ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት ድንበር ላይ በተስተዋለው የፀጥታ ችግር ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ የተከሰተው ግጭት የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት የማይጎዳ መሆኑን እና ግንኙነቱም ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከሱዳኑ አቻቸው ኤል ዲልደሪ ሞሃመድ አህመድ ጋርም ተገናኝተው ተወያይተዋል። ውይይቱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንዳለ በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከድንበር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በሙሉ ለመቅረፍ ትሰራለች ብለዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ የሚነሱ ችግሮች እንዲፈቱ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ መግለፃቸውንም ዶክተር ወርቅነህ ተናግረዋል። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርም በድንበር አካባቢ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ ተፅእኖ በማይፈጥር መልኩ ለመፍታት እንደሚሰሩ አስታውቀዋልም ብለዋል። የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤል ዲልደሪ ሞሃመድ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና የሱዳኑ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የእናቶች ዋይታ! በመተማ ሆስፒታል! ቤተሰቦቻቸው ቁስለኞችን ገብተው መጠየቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል።

የሱዳን ሰራዊት ከትህነግ/ህወሓት ጋር በመተባበር በአማራ ገበሬዎች ላይ በፈፀመው ወረራ የቆሰሉት ገበሬዎች ገንዳውሃ ከተማ መተማ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ገብተዋል። ሆኖም ቤተሰቦቻቸው ቁስለኞችን ገብተው መጠየቅ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። የእናቶች ዋይታ! በመተማ ሆስፒታል! የደርግን መውደቅ ካስደስታቸው መከካል እናቶች ይቀድማሉ። “ዘመቻ የለም፣ ገፈፋ የለም፣ ጦርነት የለም” ይሉ ነበር። ልጆቻቸው ወደ ጦር ሜዳ በግድ ዝመቱ የተባሉባቸው እናቶች። ይህን ካሉ ግን ቆይተዋል። ዛሬም ቢሆን ጦርነት አለ። ዛሬም ከደርግ የባሰ ጭራቅ ሀይል አለ። ዳር ድንበሩን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ። ዳር ደንበሩን አሳልፎ ከሰጠው ጠላት ጋር ሆኖ ንፁሃንን በከባድ መሳርያ የሚጨርስ ጭራቅ ሀይል አለ። ከደርግ የባሰ! ይህ የምታዩት ፎቶ ዛሬ የተነሳ ነው። ገንዳውሃ ከተማ መተማ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው። ትህነግ የሱዳን ጦርን መርቶ ቤተሰባቸውን በከባድ መሳርያ ያስመታባቸው እናት ሲያለቅሱ የሚያሳይ ነው። አንድ አባት ሊያፅናኑዋቸው ሲጥሩ ያሳያል። ትህነግ የከፈለው የሱዳን ጦር ደንበር ጥሶ ሲመጣ የኢትዮጵያ የሚጠብቅ ጦር አልነበረም። የሱዳኑንም፣ የኢትዮጵያ ነው የሚባለውንም የሚመሩት ትህነጎች ናቸው። እናቶች ደግሞ ዋይታቸውን ለማንም ማሰማት አይችሉም። ወራሪውም አስወራሪውም ጠላት አድርጎ ፈርጇቸዋል። ደርግ እንኳን ወደቀ ያሉ እናቶች ከደርግ የባሰ ጭራቅ ጥሎባቸዋል። ዛሬም ዋይታቸው ቀጥሏል! የሱዳን ጦር በአማራ ገበሬዎች ላይ የከፈተው ጦርነት የጀመረው ሰኔ 25/2010 ዓም ነው የሚባለው ስህተት ነው። ሰሚ ጆሮ አጥቶ ነው እንጅ ወረራው በአዲስ መልክ ወረራው ከጀመረ ከ25 ቀን በላይ ሆኖታል። ማስተካከያ የሚያስፈልገው ባለፉት ሶስት ሳምንታትም በርካታ ገበሬዎች ስለተገደሉ፣ ስለቆሰሉና ስለጠፉ ነው! ይህ ሁሉ
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ (ጌታቸው ሺፈራው)

ከሱዳን ወረራ ጀርባ ያለው የትህነግ/ህወሓት ሴራ ሲጋለጥ (ጌታቸው ሺፈራው) ከሶስት ቀን በፊት ሱዳን ውስጥ የሚኖሩ የወልቃይት አማሮች ከሚቀርቧቸው የሱዳን ባለሀብቶች አንድ መረጃ ይደርሳቸዋል። በአንድ ወቅት ባዕከር የሚባል ቦታ መምህር የነበርና በወልቃይት አማሮች ላይ ጥቆማ እያደረገ በማሳሰር ለትህነግ በዋለው ውለታ ትህነግ የፀጥታ ኃላፊ ያደረገው ተኪ ተኩ በአዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች ቅስቀሳ ሲያደርግ እንደሰነበተ ይነግሯቸዋል። ይህን ጉዳይ እኔም ትናንት ምሽት ዘግቤው ነበር። ተኪ መተኩ ትህነግ ምዕራብ ትግራይ የሚለው ወልቃይት ዞን ፀጥታ ኃላፊ ሲሆን ገዳዲፍ፣ ገላባትና አዋሳኝ የሱዳን አካባቢዎች በመዞር የትህነግ ደህንነቶች ጋር በመሆን የአማራ ገበሬዎች ላይ ጦርነት እንዲከፈት ሲያደራጅ ሰንብቷል። የሱዳን ባለሀብቶች ለሱዳን ጦር ቀለብ እስከቻሉ ድረስ የጠየቁት የሰራዊት ይሰጣቸዋል። የዚህን ውጊያ ዋጋም ተኪ የተባለው የትህነግ የፀጥታ ሀላፊ ገንዘብ ከፍሎ መመለሱን የሱዳን ባለሀብቶች ለወልቃይት ተወላጆች ተናግረዋል። በጉዳዩ መሳተፍ ያልፈለጉት ባለሀብቶች “ከእናንተ ጋር ሊያጋጨን ነው” ሲሉ ቀድመው አሳውቀዋል። የትህነግ የዞን ፀጥታ ሀላፊ ተኪ አስተባባሪነት የተደረገው ዝግጅት ሲጠናቀቅም፣ ለትህነግ ተባባሪ በሆኑ ባለሀብቶች በኩል በሶስት አቅጣጫ ጦርነት ተጀምሯል።በቋራ፣ በመተማ ቁጥር አንድ እና በጓንግ በኩል የታቀደው ጦርነት በቋራና በመተማ በኩል ተጀምሯል። በቋራ በኩል የአማራ ገበሬዎች አንድ የሱዳን ፓትሮልን መማረክ ሲችሉ፣ በመተማ በኩል የተከፈተ ጦርነት የብዙ ገበሬዎችን ህይወት ቀጥፏል። በጓንግ በኩል ገበሬዎች ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተዘጋጀ የሱዳን ጦር እንዳለ ታውቋል። በአማራ ገበሬዎች ላይ ጥቃት እየፈፀመ ያለው የሱዳን ሰራዊት ከባድ መሳርያ የታጠቀ ሲሆን ገበሬዎቹ ያዙት አጭር ርቀት መሳርያ ነው።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት በአሶሳ ሲነቃበት በሱዳን በኩል በአማራ ገበሬዎች ላይ የውክልና ጦርነት ጀምሯለ 

በሱዳን ጦር ከባድ መሳርያ ተኩስ ተከፍቶባቸው የቆሰሉት አማራ ገበሬዎች ገንዳውሃ የሚገኘው መተማ ሆስፒታል ገብተዋል።እስካሁን በሁለት አንቡላንስ የመጡ ቁስለኞች ወደ ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል። ሕወሓት በአጋዚ አልበቃውም! በአልበሽር ጦር የአማራ ገበሬዎችን እያስጨፈጨፈ ነው። በአሶሳ ሲነቃበት በሱዳን በኩል የውክልና ጦርነት ጀምሯል። በአማራ ገበሬዎች ላይ! የአማራ ገበሬዎችን እያስጨፈጨፈ ያለው ትህነግ ነው ከሱዳን ሰራዊት ጋር ሆኖ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ ያለው ህወሓት መሆኑን ቁስለኞቹ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የመጣው የሱዳን ጦር ጋር ገጥመው የቆሰሉት በግልፅ ተናግረዋል። የገጠማቸው ሕወሓት ነው። እነሱ የሕዝብ ስም ጠርተው ነበር የተናገሩት። ላኪው ትህነግ/ህወሓት ነው በሚል ነው። ጦርነቱን መርቶ የአማራ ገበሬዎችን እየጨፈጨፈ ያለው ትህነግ/ህወሓት ነው! ከቁስለኞቹ ባሻገር የልዩ ሀይሉ ሃላፊ ለገንዳውሃ ኃላፊዎች ጦርነቱን እየመራው የሚገኘው ሕወሓት ነው ብሏል። ገንዳውሃ ሆስፒታል 7 ቁስለኞች ገብተዋል አምስቱ ገበሬዎች ሲሆኑ ሁለቱ በሱዳን መከላከያ እና በገበሬዎቹ መካከል “ሽምግልና” አርፍዶ ዘግይቶ የገባው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ናቸው። ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ገበሬዎች እንዳሉ ታውቋል። ሁለቱ የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ወደ ጎንደር ሆስፒታል እንዲላኩ “ሪፈር” እንደተባለላቸው ተገልፆአል። ከደደሎ ወደ ገንዳውሃ የሚመጡ ተጨማሪ ቁስለኞች እንዳሉ ተገልፆአል። ብዙ ቁስለኞች ሸኸዲ ሆስፒታል ገብተዋል! ከቆሰሉት ገበሬዎች መካከል አበጀ አንዱ ነው። አበጀ የ37 አመት እድሜ ያለው ሲሆን ቋራ ወረዳ ቁጥር አራት ነፍስ ገበያ አካባቢ ነዋሪ ነው። ከሱዳን ሰራዊት በተተኮሰ ከባድ መሳርያ ብዙ አማራ ገበሬዎች ተገድለዋል። ቆስለዋል። የሱዳን ሰራዊት የሁለት ገበሬዎችን አስከሬን ወደኋላ አሽሽቷል። የጠፉ ገበሬዎች እንዳሉም ታውቋል። የአማራ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በሱዳን ጦር እና በጎንደር ገበሬዎች መካከል ጦርነቱ ተፋፍሟል።

“መንግስት” አልባው ሕዝብ ከሱዳን ጋር ሊገጥም ነው (ጌታቸው ሽፈራው) ባለፉት ሳምንታት የሱዳን ጦር በአማራ ገበሬዎች ላይ ጦርነት ከፍቷል። ትናንት ሰኔ 25/2010 ዓም ገበሬዎች ከሱዳን ሰራዊት ጋር ውሏቸውን ሲታኮሱ ውለዋል። የሱዳን ጦር አፈና የፈፀመባቸውን 70 ያህል ገበሬዎች ነፃ ለማውጣት በተደረገ ጦርነት ብዙ ገበሬዎች ተገድለዋል። ቆስለዋል። በጦርነቱ የተሰውት ላቀው ሰለሞንና ገብሬ አውለው አስከሬን ወደ ቤተሰብ ሲላክ ከአምስት በላይ ገበሬዎች ቁስለኛ ሆነዋል። የአቶ ለቀው ሰለሞን እና የገብሬ አውለው መገደል ከተሰማ በኋላ የመተማ፣ የሸህዲና የአርማጭሆ ህዝብ ከሱዳን ጦር ጋር ለመግጠውም መወሰኑ ተሰምቷል። በዛሬው ዕለት የመተማ ነዋሪዎች በአይሱዚ መኪና ጦርነት ወደተነሳበት ደለሎ እየሄዱ መሆኑን ገልፀውልኛል። የ”ኢትዮጵያ መከላከያ” ሰሞኑን ወደ ደንበር ቢጠጋም የኢትዮጵያ ገበሬዎች በሱዳን ጦር ሲዘመትባቸው ዳር ዳር ተመልካች ሆኗል። ዛሬ ሰኔ 26/2010 ዓም የአማራ ልዩ ሀይል ከሕዝቡ ጋር ወደ ደለሎ መሄዱም ተጠቁሟል። የአማራ ገበሬዎች የሀገር ዳር ድንበር ጥሶ የመጣው ጦር ጋር ፊት ለፊት ገጥመው የመከላከያ ሰራዊቱ ከድንበር ርቆ ከርሟል። መንግስት ነኝ የሚል አካልም ሆነ ስለ ሀገር ዳር ድንበር ያገባኛል የሚል አካል ስለ ገበሬዎቹ ሞት ጆሮ አልሰጡም። የአማራ ገበሬ የድጋፍ ሰልፍ ሲወጣ ኢትዮጵያዊ ይባል፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በቃታ ብረት እየጠበቀ ሲሰዋ ግን ሞቱን የሚያወራ የለም። በወራሪ ጦር ሲገደል አማራ ነው!
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሰብል አወደመ

የሱዳን ሰራዊት የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ሰብል አወደመ (ጌታቸው ሺፈራው) የሰሜን ሱዳን ወታደር የኢትዮጵያ አርሶ አደሮችን ሰብል ማውደሙን ነዋሪዎች ገልፀዋል። ትናንት ሰኔ17/2010 ዓም ዲሽቃና መትረየስ ጨምሮ ከባድ መሳርያዎችን ታጥቆ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት የገባው የሱዳን ጦር ከኢትዮጵያ ገበሬዎች ጋር ተኩስ መግጠሙ ተገልፆአል። የሱዳን ጦር በመተማ ወረዳ አቲሚቲ የተባለ ቦታ የገበሬዎችን ሰሊጥ ማሳ በትራክተር በማረስ ያወደመ ሲሆን ለአብነት ያህልም መከተ እና ማርቆስ የተባለ ገበሬዎች ማሳ መውደሙ ታውቋል። የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ከተሰጠ በኋላ ድንበሩን መጠበቅ ያቆመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ሰኔ 18/2010 ዓም ከቦታው በመድረስ የኢትዮጵያ ገበሬዎችን ወደኋላ እንዲመለሱ አድርጓል ተብሏል። በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት በቋራ ወረዳ በሱዳን ጦርና በገበሬው መካከል ተኩስ እንደነበር ተገልፆአል። መሬታቸው ለሱዳን የተሰጠባቸው ገበሬዎች መሬቱን በኪራይ ሲያርሱ የቆዩ ሲሆን ከ2008 ዓም ጀምሮ “በራሳችን መሬት ኪራይ አንከፍልም” በማለታቸው ከሱዳን ጦር ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈፀምባቸው ቆይቷል። በአንፃሩ የኢትዮጵያ ጦር ድንበሩን በመጠበቅም ሆነ ገበሬዎችን ከሱዳን ጦር ጥቃት በመከላከል ተግባር ላይ እንዳልሆነ ተጠቁሟል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢትዮጵያና ሱዳን አሲረውብኛል ሲል የኤርትራ መንግስት ወነጀለ

የኢትዮጵያና የሱዳን መሪዎች በቅርቡ በካርቱም ባደረጉት ስብሰባ ላይ አሲረውብኛል ሲል የኤርትራ መንግስት የከሰሰ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ ክሱን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ነው ብሎታል፡፡ የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት የኢሳያስ አፈወርቂን መንግስት ከስልጣን ለማስወገድ፣ የፕሬዚዳንቱን ተቃዋሚዎች ለመደገፍ ተስማምተዋል፤ በሀገሪቱ መንግስት ላይ አሲረዋል” ብሏል፡፡ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በካርቱም ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሽር ጋር ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ መስማማታቸውን የጠቀሰው የኤርትራ መንግስት፤ በዚህም የኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎችን ለመደገፍ ተስማምተዋል ብሏል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በድንበራቸው አካባቢ ነፃ የንግድ ቀጠና ለመመስረት መስማማታቸውም ለዚህ ማሳያ ነው ብሏል የኤርትራ መንግስት መግለጫ፡፡ አዲስ አድማስ ያነጋገራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም፤ በበኩላቸው “የኤርትራ መንግስት ክስ መሰረተ ቢስ ውንጀላና አስቂኝ የፈጠራ ድራማ ነው ብለዋል፡፡ የኤርትራ መንግስት በአሜሪካ የተጣለበትን ማዕቀብ ለማንሳት የሚያስችል በጎ እርምጃ አለመታየቱን የጠቆሙት የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ፤ የኤርትራ መንግስት የባህሪ ለውጥ ለማምጣት እስካሁን ፍንጭ አለማሳየቱን ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በበአለ-ሲመታቸው ወቅት ለኤርትራ መንግስት የእርቅ ጥሪ ማቅረባቸውን በመግለጫው የጠቀሰው የኤርትራ መንግስት፤ “የተለመደ የህዝብ ግንኙነት ስራ ነው፤ ይህን ጥሪ ማቅረባቸው አዲስ ነገርም አስደናቂም አይደለም” ብሏል፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook