አል-ፋሽጋ ዳግም በኢትዮጵያውያን እጅ ገባ
ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት በትግራይ ክልል የህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ በነበረበት ወቅት የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም፣በሱዳን ጦር ተወርሮ የነበረው ሰፊና ለም መሬት፣ አሁን በጀግኖች ኢትዮጵያውያን ገበሬዎችና ሚሊሻዎች ቁጥጥር ስር ውሏል።
የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የመተማና የቋራ ወረዳ ለም መሬቶችን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።
በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ መንግሥትም ችግሩን በዲፕሎማሲና በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡
በዚህ የሱዳን ወረራ ወቅት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከእርሻቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብልና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው አይዘነጋም፡፡
የሱዳን ባለሥልጣናት ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው ሲሉ መክሰሳቸው ተዘግቦ ነበር፡፡
andafta