Blog Archives

ዶክተር አብይ ቃሉን በልቷል (ጌታቸው ሺፈራው)

ዶክተር አብይ ቃሉን በልቷል (ጌታቸው ሺፈራው ~ክፍል 1)   ዶክተር አብር አህመድ መቀሌ ላይ ስለ ወልቃይት በተናገረው ያልተገባ ነገር ተቃውሞ ሲሰማበት ሚያዝያ ወር መጀመርያ ወደ ጎንደር መጥቷል። ጎንደር ጎሃ ሆቴል በነበረው ስብሰብ ከተነሱለት ጥያቄዎች አንዱ ለሱዳን ስለ ኢትዮ_ሱዳን ድንበር ነበር። በወቅቱ የሰጠው መልስም “ነገ አልበሽርን አገኘዋለሁ። ተገናኝተን እናወራለን።… …በቅርቡ የሕዝቦች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይገታ እናደርጋለን” የሚል ቃል ገባ። ሕዝብም ችግሩን ያውቀዋልና አጨበጨበ። ዶክተር አብይ አልበሽርን ባህርዳር በነበረው የጣና ፎረም አገኘው። በጥቂት ቀን ውስጥ “መፍትሄ እንሰጥበታለን፣ ሕዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲቀጥል ይሆናል” ካለ ከሶስት ወር በኋላም የሱዳን ሰራዊት የአማራ ገበሬዎች ላይ ከባድ መሳርያ እየተኮሰ፣ ድንበር ጥሶ እየገባ ነው። ሰኔ 4/2010 ዓም በተጠናከረ ሁኔታ የጀመረው የሱዳን ወረራ የእነ ዶክተር አብይን ትኩረት አላገኘም። ከሰኔ 4/2010 ዓም ጀምሮ ገበሬዎች ታፍነው ወደ ሱዳን ተወስደዋል፣ አራት ሰራተኞችና አንድ ባለሀብት እርሻቸው ላይ እያሉ ተገድለዋል። የገበሬዎች ማሳ በሱዳን ሰራዊት ወድሟል። ካምፓቸው ተቃጥሏል። ከአስር ቀን በፊት በተደረገ ወረራ ከ7 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። በሁለተኛው ቀን መከላከያ ሰራዊቱ ወደ ቦታው ቢያቀናም “ከቻላችሁ ገበሬውን አረጋጉ፣ ካልሆነ ተመለሱ” የሚል ትዕዛዝ ሲሰጣቸው ገበሬውን ያገዙት ከትዕዛዝ ያፈነገጡ የተወሰኑ አባላቱ ብቻ ነበሩ። የሱዳን ሰራዊት በከባድ መሳርያ፣ የአማራ ገበሬ በነፍስ ወከፍ መሳርያ ጦርነት ሲገጥሙ ዳር ድንበርን ለማስጠበቅ ግዴታ ያለበት፣ ከሶስት ወር በፊት ” በቅርብ ቀን ሕዝብ ሰላማዊ ኑሮውን እንዲኖር እናደርጋለን” ያለው አብይ መንግስት ያደረገው ነገር አልነበረም። ገበሬው በሱዳን ጦር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የተሰራው ግፍ ሲጋለጥ ፦ ቪድዮ

Video – ከቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች ላይ የተሰራው ግፍ እና መንግስታዊ ሕገወጥነት ሲጋለጥ $bp("Brid_10652_1", {"id":"12272","stats":{"wp":1},"title":"Amhara displacement","video":"223941","width":"550","height":"309"});
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News