Blog Archives

የአብዲ ኢሌ ቀኝ እጆች ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ ፤ ለቀማው ቀጥሏል።

የአብዲ ኢሌ ቀኝ እጆች ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ ፤ ለቀማው ቀጥሏል። የአብዲ ኢሌ የሚዲያ አማካሪና የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊ ድሬዳዋ ላይ ከተሸሸጉበት ተያዙ። ከስልጣን አልወርድም በማለት ከፍተኛ የሃገር ክሕደት የፈጸመው አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ የሚዲያ አማካሪው የነበረው መሃመድ ቢሌ ድሬዳዋ ውስጥ ከተሸሸገበት በቁጥጥር ስር ውሏል።ግለሰቡ በተጨማሪ የሙያና ቴክኒክ ስልጣና ኃላፊ ሆኑ ክልሉን ያገለግላል። በተጨማሪም የጸጥታ ጉዳዮች ሃላፊና በድሬዳዋ የአብዲ ኢሌ ወኪል ሞሃመድ አሕመድ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል። ግለሰቦቹ የሶማሌን የሃገር ሽማግሌዎች በመግደልና በማሰር የሚታወቁ ሲሆን የውጪ ምንዛሬም በኮንትሮባንድ በማመላለስ የ አብዲ ኢሌን ትእዛዝ የሚያስፈጽሙ ቀንደኛ ወንጀለኞች መሆናቸው ታውቋል። ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦላቸው አፈናንና ግድያን በድሬዳዋና በ አከባቢው ማስፈጸማቸው ማስረጃ መንግስት ስላገኘባቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። በተጨማሪም የቀድሞ የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የ አሁኑ የልማት ፕሮጄክት Pastoral Community Development Project (PCDP) ኃላፊ አብዲሃኪን ኤግል ቤቱ የተበረበረ ሲሆን እስካሁን የተሸሸገበት ባለመገኘቱ የደሕንነትች እያሰሱት ይገኛል። RAJO NEWS Arrests and house searches made in Dire-Dawa – We are getting reports from reliable sources that Mohamed Bille “Miig”, head of Technical and Vocational Training (TVeT) and Media Advisor to former regional president Abdi Iley is arrested today in Dire-Dawa. – The house of Abdihakin Egal was searched. Mr. Abdihakin was former VP and now the current head Pastoral Community Development Project (PCDP). – Mohamed Ahmed, Diredhaba Security
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በድሬዳዋ በተከሰተው ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ

በድሬዳዋ በተከሰተው ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ በትናንትናው ዕለት በድሬዳዋ ከተማ 09 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በተከሰተው ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ከሟቾቹ መካከል አራቱ ታዳጊ ህጻናት ናቸው። በግጭቱ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውንና የንብረት ጉዳት መድረሱን የገለጸው ፖሊስ በውል ያልታወቁ ዜጎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል። ግጭቱን እንዲከሰት አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ፖሊስ ገልጿል። አሁንም ግጭት ለመቀስቀስ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውን የከተማይቱ ፖሊስ የገለጸ ሲሆን እነሱን ለህግ ለማቅረብ እየሰራሁ ነው ብሏል። ፖሊስ ከተማዋን ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ቢሆንም አሁንም ሙሉ በሙሉ አለመረጋጋቷን ገልጿል። የግጭቱ መንስኤ እያጣራ መሆኑንም የአስተዳደሩ ፖሊስ ገልጿል።  
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የድሬዳዋ ሕዝብ ከዶ/ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ ጋር ተደምሮ ዋለ ።

አዲስ ቸኮል ድሬዳዋ ዛሬ ሽር ብትን ስትል ውላለች፡፡ የኢትዮጵያ ባለኮከቡና ልሙጡ፣ የኦነግ፣ የኦሮሚያ የኦህዴድ፣ የኢሶህዴፓ፣ . . . ሰንደቅ አላማዎች ተደምረው ውለዋል፡፡ የሰውን ጎርፍ ስቴዲዬም መቻል አቅቶት ከስቴዲዬም ውጪ የፈሰሰው የሰው ቁጥር የትየለሌ ነበር፡፡ ሶማሌውም፣ ኦሮሞውም፣ አማራውም፣ ጉራጌውም ፣ ትግሬውም፣ . . . . እኔ የማውቃቸው ሁሉም በደስታ ያበዱ ነበሩ፡፡ ኑሮ የጎዳው ዜጋ ሳይተርፈው ጥሩ ጅምር ያሳዩትን ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማመስገን የ200 መቶ ብር ቲሸርት ገዝቶ ከሰው ጋር እየተጋፋ፣ ፀሐይና አቧራ እየጠጣ በእግሩ ብዙ ርቀት ተጉዞ ድጋፍ ሰልፍ የወጣን ነዋሪ ማመስገን በጣም ያንሳል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩና ካቢኔዎቻቸው ላይ የሚፈጥረው ስሜት ከባድ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ ድሬዳዋ ከሰልፍ መልስ እንዲህ ሆነ፤ አንድ ጥቁር የለበሰች ሴት ፀጉሯ እንደመንጨብረር ያለ (ከሌሎች በሰማሁት ገለፃ መሰረት) የአንዳንዶችን ትኩረት ትስብና “ነይ ቦርሳሽን አስፈትሺ” ትባላለች፤ “አላስፈትሽም” ትላለች፡፡ የአዲስአበባው ትራጀዲ ከሁሉም አእምሮ አልጠፋምና ወጣቶች ወደእርምጃ ይገባሉ (ትንሽ ሳይመቷት አይቀርም እንደሰማሁት)፡፡ ወዲያው ፖሊስ አፋፍሶ ራስ ሆቴል ያስገባታል፡፡ ሰልፉ ያለቀው አራት ሰዓት ገደማ ነው፤ ቀኑ እሁድ ነው ስራም የለም፤ መቀመጥ ለፈለገም ሰዓቱ ገና ነው፤ እናም አንዳንዶቹ ለወሬ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ የምር ሴትዮዋ ተመርምራ ቦምብ መያዝ አለመያዟን ለማረጋገጥ፣. . . . . ሰው ሲሰበሰብ፣ ሲሰበሰብ፣ . . . መጨረሻ ላይ ራስ ሆቴል ዙሪያውን ዋና የሰልፉ ማዕከል ሆኖ ቁጭ! ወጣቶች ሌባ! ሌባ! እያሉ ይዘምራሉ፡፡ እኔ ከሰዎች ጋር ተቀላቅዬ ወሬ እየሰማሁ ነው፤ በእርግጠኝነት ቦምብ ይዛ አይተናታል እያሉ የሚያወሩም
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News
Follow us on Facebook
Follow us on Facebook