በኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚው ከፓርላሜንታዊ ስርአት ወደ ፕሬዚዳንታዊ ስርአት ሊለወጥ ነው

ኤሊያስ መሠረት

በኢትዮጵያ የስራ አስፈፃሚውን በጠ/ሚር ከሚመራ (parliamentarian) ወደ ፕሬዝደንታዊ (presidential) ስርዐት የመለወጥ ሂደት መጀመሩ ተሰምቷል።

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡ ሰሞን በስፋት ይነሳ የነበረው ይህ የፕሬዝደንታዊ ስርዐትን የመዘርጋት ሂደት አሁን ከታሰበው የህገ መንግስት ማሻሻያ ጋር አያይዞ በስፋት ስለተሄደበት በቅርብ ግዜያት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ የደረሰኝ መረጃ ይጠቁማል።

በፓርላመንታዊ ስርዐት ዜጎች የመረጧቸው የህዝብ ተወካዮች ጠ/ሚሩን ሲመርጡ በፕሬዘደንታዊ ስርዐት ደግሞ ዜጎች በቀጥታ ፕሬዝደንት የሚሆነውን ይመርጣሉ።

@EliasMeseret