በድሬዳዋ ባሕርዩ የተለወጠ የደንጌ ትኩሳት ወረርሽኝ ጉዳት እያደረሰ እንደኾነ ተጠቆመ

በድሬዳዋ፣ ባሕርይው የተቀየረ የደንጌ ትኩሳት ወረርሺኝ፣ በከተማ አስተዳደሩ በርካቶችን ለከፋ የጤና ችግር እየዳረገ እንደኾነ ተገለጸ። 

የጤና ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ አስቀድሞ ከሚታወቁት የደንጌ ትኩሳት ምልክቶች የተለዩ፣ ሁለት ዐይነት የበሽታው ምልክቶች እየታዩ ናቸው፡፡ በዚኽም በርካቶች እንደቀድሞው፣ በየቤታቸው ራሳቸውን ከማስታመም ይልቅ፣ በጤና ተቋማት አልጋ ይዘው ለመታከም…