ታጋቾች ወደ ጋዛ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ከስፍራው የተገኘ ቪዲዮ ማሳየቱን እስራኤል አስታወቀች

ሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለችውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) የመከላከያ ሰራዊቱ አሳይቷል።
ከታጋቾቹ አንዷ የሆነችውም ወታደር በሆስፒታሉ መገደሏን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃለ አቀባይ ተናግረዋል።
የ19 ዓመቷ ኖአ ማርሲያኖ የተገደለችው ቀላል ጉዳት ደርሶባት ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋ…