የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ የሆኑት መምህር ተሾመ በየነ በጸጥታ አካላት ተወሰዱ !

የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ የሆኑት መምህር ተሾመ በየነ በጸጥታ አካላት ተወሰዱ !

++++

በቋሚ ሲኖዶስ መልካም ፈቃድ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም የተቋቋመውን ሀገር አቀፍ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ አስተባባሪ ዐቢይ ኮሚቴ በጸሐፊነት እንዲያገለግሉ ተመድበው የነበሩት መምህር ተሾመ በየነ በዛሬው ዕለት በጸጥታ አካላት ተወስደዋል።

መምህር ተሾመ የጴጥሮሳውያን ኅብረት ጸሐፊ ሲሆኑ ኅብረቱን ወክለው በተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ውስጥ በከፍተኛ ኃላፊነት ቤተክርስቲያንን እያገለገሉ የነበሩ ወንድም ናቸው።

በዛሬው ዕለት ከቅዱስ ዑራኤል አካባቢ የጸጥታ አካላት ነን በሚሉ ግለሰቦች የተወሰዱት መምህር ተሾመ በአሁኑ ሰዓት የተወሰዱበት ቦታ እንደማይታወቅ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

መምህር ተሾመ ከዚህ በፊት ከዐቢይ ኮሚቴው አባላት ጋር በጋራ በመሆን በማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በኩል መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ሲሆን ከዐቢይ ኮሚቴው በጸጥታ አካላት የተወሰዱ ሁለተኛው ሰው ሆነዋል ሲል ማኅበረ ቅዱሳን ዘግቧል። ምንጭ፦ ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል