የትግራይ የጤና አገልግሎት መሻሻል

በትግራይ ጤና ቢሮ ገለፃ መሠረት ሙሉ በሙሉ ከወደሙ የጤና ተቋማት ውጭ የተቀሩትን ወደ መደበኛ የጤና አገልግሎት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።በመድኃኒትና የሕክምና ቁሳቁስ አቅርቦት በኩል መሻሻሎች ቢኖሩም ከፍላጎት አንፃር ግን አሁንም ብዙ እንደሚቀር የክልሉ ጤና ቢሮ ይገልፃል። አሁንም ቢሆን የሕክምና ግብአቶች አቅርቦት ውሱንነት አለ ይላል።…