እስከ 18 ዓመቱ ድረስ ማንበብ እና መጻፍ ሳይችል የቆየው ያሰን፣ አሁን በኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ በእድሜ ትንሹ ጥቁር ፕሮፌሰር ለመሆን በቅቷል። ያሰን አርዴይ በሦስት ዓመቱ በተደረገ ምርመራ ነበር የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት እንዳለበት የታወቀው። በዚህም ምክንያት እስከ 11 ዓመቱ ድረስ መናገር አይችልም ነበር። የ37 ዓመቱ ያሰን በአሁኑ ወቅት በእውቁ ኬምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የሶሲዮሎጂ ፕሮፌሰር ሆኗል።…