ከ0.50$ ወደ 1.20$ በሁለት ወር አድገናል፣ ግን ብዙ ይቀረናል #ግርማካሳ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ከአንድ ሳምንት በፊት በዳያስፖራ ፈንዱ የተሰበሰበው ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ብቻ ነበር። ወደ ሶስት ሚሊዮን ዳያስፖራ ይኖራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። ግን ቁጥሩን አሳንሰን አንድ ሚሊዮን ነው ያለው ብንል እንኳን በቀን አንድ ዶላር ሳይሆን በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም የማዋጣት ያህል ነበር ። አሁንም በጣም፣ እጅግ በጣም ትንሽ ነበር።

ባለፉት አስር ቀናት ግን የተሰበሰበው ገንዘብ ቁጥሩ ወደ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ደርሷል።፡ በሶስት እጥፍ ነው ያደገው። ይሄ ትልቅና አስደሳች ለዉጥና ስኬት ነው።

ሆኖም ቁጥሩ አሁንም መሰብሰብ ካለበት በጣም ያነሰ መሆኑን ላሰምርበት እወዳለሁ። በሁለት ወር አምሳ ሳንቲም ከመሰብሰብ ፣በሁለት ወር አንድ ብር ከሃያ ሳንቲም ወደ መሰብሰብ ነው የተሸጋገርነው። በአጠቅላይ አሁን መሰብሰብ ከነበረበት ሰባ ሁለት ሚሊዮን ዶላር፣ አንድ ነጥብ አምስት አካባቢ ብቻ መሰብሰቡ፣ መሰብሰብ ካለበት ሁለት ከመቶ ብቻ መሰብሰቡን የሚያሳይ ነው።

አዎን ከግማሽ ሚሊዮን ወደ አንድ ነጥብ ግማሽ ሚሊዮን መድረስ ትልቅ መሻሻል ነው። ግን አሁንም እዚያው ገና እየተንፏቀቅን በመሆናችን እንደ ኢሊ ሳይሆን እንደ ጥንቸል ወደ ፊት ትልቅ እርምጃ የምንራመድበትን አሰራር ማስቀመጥና ተግባራዊ ለማድረግ መነሳት አለብን።

– ከዚህ በፊት ደጋግሜ ጽፌዋለሁ፣ የትረስት ፈንዱ የቦርድ አባላት በጥቅሉ ገንዘብ አዋጡ ሳይሆን ፕሮጀክቶችን ነድፈው፣ በዚህ አመት እነዚህን ነው የምናደርገው ብለው ያቅርቡልን። ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ማስቀደማቸው ለገንዘብ ማሰባሰቡ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል።

– ኮሚቴው በየከተማው ያሉ የእምነት ተቋሟት፣ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበራት ጋር በጉዳዩ ላይ ይምከሩ። ከነርሱ ጋር አብሮ የሚሰሩበትን ፕሮቶኮል ቢያመቻቹ ጥሩ ነው። አዲስ ቻፕተር መመስረት ጥሩ ሊሆን ይችላል። ግን ኦልሬዲ የተመሰረቱ ተቋማት ካሉ ፤ ከነርሱ ጋር መስራቱ ጥሩ ሊሆን ይችላል።

– ሌላው አዲስ አምባሳደር በአሜሪካ ስለተሾመ፣ ኤምባሲውም በዚህ ረገድ ማገዝ የሚችልበት ሁኔታ ቢኖር ጥሩ ነው።

– አንድ ሰው ሲነግረኝ ቮሎንተር ለማድረግ ስሙን አድራሻዉን ኢሚሉን ከሁለት ወር በፊት አሳውቁቆ፣ በዳያስፒራ ትረስት ፈንድ ድህረ ገጽ ላይ፣ የዳያስፒራ ትረስት ፈንዱ ኮሚቴው ግን እስከ አሁን ኮንታክት እንዳላደረገው ነው የነገረኝ። ለመርዳት የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን በተቀላጠፈ መልኩ ማስተናገድ ካልተችለ የተፈለገዉን ግብ ማሳካት አይቻልም።

ወገኖች፣ አቅም አለን። እንችላለን። ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን በቀን አንድ ዶላር ከመደብን፣ ሶስት መቶ ስድሳ አምስት ሚሊዮን ዶላር ወይንም አስር ቢሊዮን ብር መሰብሰብ እንችላለን።

ሁሉንም ነገር የትረስት ፈንዱ ኮሚቴ ላይ መጣል የለብንም። የት ገንዘብ ማዋጣት እንደሚችሉ በመግለጽ ዘመዶቻችንንና ደኞቻችንን እንዳይረሱ እንዲያዋጡ እናበረታታ። እስቲ ቻለንጅ አድርገን እንውሰድና የሚቀጥለው አንድ ወር ቢያንስ አስር ሰዎችን አነጋገረን፣ ራሳቸውንን እንደ ቦርድ አባል አድርገን ቆጥረን፣ ግደታቸውን እንዲወጡ እናድርግ። በቃ የኛው የግላችን ጉዳይ አድርገን እንረባረብበት። ደግሞም የኛው ጉዳይ ነው።