ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ድንገተኛ ሞት በስተጀርባ የጠላት እጅ ይኖር ይሆን? አብረን የምናይ ይሆናል!

ጋዜጠኝ ደምስ በለጠ ከመሞቱ ዋዜማ የነበረውን ውሎ አባይ ዘውዱ እንደሚከተለው ዘግቧል

የታህሳስ 12 ቀን ውሏቸውን በተመለከተ ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ይህን ይመስላል – (ለምርመራው ከጠቀመ)

1. ረፋድ 4 ስዓት ላይ ፒያሳ ቀጠሮ አለኝ ብለው መነን ት/ቤት አካባቢ ካለው ከእናታቸው ቤት ወጡ፣

2. 4 ስዓት ላይ ከቤት እንደወጡ ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር እዛው መነን አካባቢ ከሰብለ አረጋ ከተባለች ቤተሰባቸው ቤት ቡና ጠጥተው፣ለ30 ደቂቃ ያህል ከቆዩ በኃላ ስልክ ሲደወልላቸው ፒያሳ የማገኘው ሰው ስላለ በኃላ እመጣለሁ ብለው ከሰዎች ተለይተው ሄዱ።(ዘመዳቸው ሰብለ አረጋ ከተናገረችው) (የተደወለላቸውን ስልክ ሳይ ልክ 4 ስዓት ከ28 ደቂቃ ላይ የደወለላቸው ደግሞ አንድ ጓደኛቸው ነው(ስማቸው ይቆየን)።በአካል ያግኛቸው በስልክ ብቻ ገና አልተጣራም።

3. ከቀኑ 6 ስዓት አካባቢ ስደውልላቸው ሩሲያ ኤግዚቪሽን አካባቢ እንደነበሩ ነግረውኛል።ማገኛቸው ሰዎች አሉ ብለውኛል። (ከእህታቸው ልጅ ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተገኘ)

4. ከቀኑ 9 ስዓት ተኩል ወደ እናታቸው ቤት ተመለሱ፣ጥሩ የጤንነት ስሜት ላይ አልነበሩም፣የቀረበላቸውን ምግብ ቀማምሰው ነው የተውት፣የድካም ስሜት አለባቸው፣የሆኑትን ነገር ብትጠይቃቸውም ስሜታቸውን አላጋሯቸውም። (እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ከተናገረችው )

5. በመሀል አቶ ወርቁ (ጓደኛቸው) እና ወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ወደ እናታቸው ቤት በመምጣት ጋዜጠኛ ደምስንና ቤተሰቡን ሲያጫውቱ ቆዩ፣ከተወሰነ ቆይታ በኃላ እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ለስራ ጉዳይ ከቤት ወጡ።

6. ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ከእናታቸው ጋር እነ ወ/ሮ እታፈራሁና አቶ ወርቁ ሲጫወቱ እስከ 12 ስዓት አካባቢ አብረው ቆይተዋል፣ነገር ግን በመሀል እንቅልፍ ያሸልባቸው የነበሩት ጋዜጠኛ ደምስ በግምት 11 ስዓት አካባቢ”ጠዋት ስለተነሳሁ ትንሽ ልተኛ”ብለው ወደ መኝታ ክፍላቸው ገቡ። (ከወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ንግግር የተወሰደ)

7. 12 ስዓት አካባቢ ከተማ ቆይተው እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና የአዜብ ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል። (ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተወሰደ)

8. ከምሽቱ 1 ስዓት ተኩል ከእንቅልፋቸው ተነስተው ከክላሳቸው በመውጣት ከቤተሰብ ጋር እራት በልተዋል። ከእራት በኃላ ከአሜሪካን አገር ከምትኖር የስራ ባልደረባቸው ጋር ስልክ ተደወለላቸው፣እያወሩ ወደ ክላሳቸው ገቡ፣ለረዥም ጊዜ አውርተዋል።ከአሜሪካን አገር ለጉብኝት አብሯቸው የመጣው የ8 ዓመት ልጃቸውም አብሯቸው ተኝቷል።

9. ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን ከረፋዱ 3 ስዓት አካባቢ “ያለ ወትሮአቸው ተኝተው አረፈዱ”በሚል(ሁሌ ከጠዋቱ 12 ስዓት ይነሱ ነበር)እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ወደ ደምስ መኝታ ይገባሉ፣በሩ ክፍት ነበር፣ሲገቡ ግን ወንድማቸው በደረት ተኝተው ደም የተቀላቀለበት ትውኪያ ሲያዩ ደንግጠው ከክላሱ በመውጣት ይጮሀሉ፣ከ20 በማይበልጡ ደቂቃዎች በርካታ የጎረቤት ሰዎች ወደ ጋዜጠኛው ክፍል ይገባሉ።ከገቡት መካከል እኔ አንዱ ነኝ ያሉት ጎረቤት አቶ ሳሙኤል አብርሀ”ደምስ በጀርባቸው ተንጋለው፣ሰውነታቸው ቀዝቅዞ ነበር፣ልጃቸውም ደግሞ መሬት ላይ ቆሞ ነበር፣ እኔ እጀን አሞኝ ስለነበር አልተሸከምኩም የተሸከሙት እንደነገሩኝ እጃቸው ይንቀሳቀስ ነበር” ሲሉ ተናግረዋል። (እጃቸው ሲንቀሳቀስ ነበር ያሉትና ተሸክመው ከመኪና አስገብተው የወሰዱት ሰዎች ተፈልገው የሚጣራ ይሆናል)

10. ወደ ጴጥሮስ ሆስፒታል ስንወስደው ሀኪሞች አስታማሚዎችን አስወጥተው 30 ደቂቃ ከቆዩ በኃላ ያለምንም ህክምና አስታማሚዎችን ጠርተው “ከሞቱ እኮ ቆይተዋል”በማለት አስከሬን መለሱልን። (እህታቸው ወ/ሮ አዜብና ጎረቤት አቶ ሳሙኤል አብርሀ)

11. አስከሬናቸው ወደ እናታቸው ቤት ተመልሶ በሳጥን ገብቷል። ከጉለሌ ክ/ከተማ የመጡ የመነን አካባቢ ፖሊሶች አንዳንድ ለመረጃው ቅርበት አላቸው ብለው ያመኗቸውን ሰዎች እያነጋገሩ መረጃ ሰብስበው ለምርመራ ክፍል ሪፖርት አድርገዋል (ከተጠየቁት መካከል አዜብ፣ አቶ ሳሙኤል፣ ህፃን ገላውዲዮስ…) በሪፖርቱ መሰረት ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ የመጡ መርማሪዎች ከቀኑ 10 ስዓት አካባቢ የጋዜጠኛ ደምስ አስከሬን ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደወሰዱ ታውቋል። አልጋቸውና ወለል ላይ ደም የተቀላቀለበት ትውኪያ ደርቋል፣ ምርመራ አልተደረገበትም።

ከአንጋፋው ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ አሟሟት ጀርባ አንዳች ሴራ ያለ ይመስላል! እንደ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ተድበስብሶ እንዳይቀር ስንል በፈጣሪ ስም ፍትህ ፍትህ ፍትህ እያልን እንለምናለን!

የሚመለከተው የህግ አካል አጣርቶ ለህዝብ እንዲያሳውቅ እንጠይቃለን! የሚዲያ ሰራተኞች ልዩ ትኩረት ሰጥታቹህ እንድትከታተሉ እንጠይቃለን!መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV