መቀሌ > አዲስ አበባ ( ናይሮቢ) > ጆሃንስበርግ ….. ሕወሓቶች ወደ ደቡብ አፍሪካ …. ፍርሐት እና ስጋት

ብዙ ብዙ ሰማን ዛሬ በሰንበት …….

May be an image of 3 people and textሕወሓቶች ወደ ደቡብ አፍሪካ አንድ ሰው ይወከል ሁለት ሰው አሊያም ሁላችንም እንሂድ እያሉ በመነታረክ ላይ ናቸው። በውጪ ያለው የሕወሃት ክንፍ ደግሞ ጥምር ጦሩ መቀሌና አዲግራት እንዳይገባ አሜሪካንን መማፀን ማስጨነቅ ይዘዋል። እንደበቅበታለን ያሉት ዋሻ ቀድሞ በጥምር ጦሩ ተይዟል። ሕወሓቶች በሰፈሩት ቁና እየተሰፈሩ ነው። የስራቸውን ሳይመሽ በጊዜ እየተጋቱት ነው ! ሕወሓቶች እዛው ደቡብ አፍሪካ ያስቀሩናል የጦር ጄኔራሎቻቸውንም በቁጥጥር ስር መቀሌ ላይ ይውላሉ የሚል ስጋታቸው ቢያይልም አሜሪካ አይዟቹ ብትልም ጉዞው ግን በፍርሃት የታጀበ ነው።

መቀሌ አዲግራት እና ….. የተባሉ ከተማከተሞች ከሕወሃት እጅ አውጥቶ ወደ ሕዝብ ለመመለስ ትግሉ ቀጥሏል። ወደ ደቡብ አፍሪካ እኔ ልሂድ እኔ የሚሉት የሕወሓት አመራሮች ጥምር ጦሩ ሰኞ መቀሌን ሊቆጣጠር ይችላል በሚል ስጋት የቆፈሩት ምሽግ ውስጥ ያስቀመጧቸው ወታደሮቻቸው ላይ እንኳን እምነት አላሳደሩም።

በጌታቸው እና ፃድቃን እየተመሩ በአሜሪካ አይሮፕላን ጅቡቲ ደርሰው የተመለሱት አዲስ አበባ ትራንዚት ያደረጉት አመራሮች ደግመው ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዳይሄዱም የጦፈ ክርክር ቢያዝም የሚሄዱት ዛሬ ይታወቃሉ ተብሏል። ደብረፂዮን ካሌድኩ እያለ ነው በዛው ሊሸበለል ይችላል በሚል ጉርሙርታ ቢበዛም አሜሪካኖቹ አይሮፕላናቸውን ትላንት ምሽቱን አስገብተውላቸዋል። አዲስ አበባ ያለም አንድ ዲፕሎማት መቀሌ ገብቷል። ትራንዚቱ ናይሮቢ ይሁን ተብሏል።

እንዲህ እንዲህ እያለ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱ ሕወሓቶችን አሜሪካ ትወስናለችም ሰምተናል። ወጣም ወረደ ሕወሓቶች የድርድር ሻማውን ሲያበሩ ጥምር ጦሩ መቀሌና አዲግራት ሲገባ እኩል እንዳይሆን አስፈርቷል። ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ወይም ናይሮቢ ትራንዚት ያደርጋሉ ፤ የደሕንነት ሰዎች ቦሌ ዙሪያ ሰፍረዋል። ደብረፂዮን እና ጌታቸው በአሜሪካን አይሮፕላን ውስጥ ይንጎባለላሉ ተብሏል። ጄኔራሎቹ መቀሌን ጠብቁ ቢባሉም ፃድቃን ምናልባት ልመናው ተሰምቶ ጆሃንስበርግ ይገኛል አሜሪካኖቹም ደቡብ አፍሪካ ላይ የሚለኮሰውን ሻማ ካኮላሹ የቴድሮስ አድሃኖምን ድንጋጤ ሳስበው ፈገግ ያሰኘኛል። የመቀሌ ዲፕሎማቲክ ወዳጆቻችንን እናመሰግናለን። #MinilikSalsawi