አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ400 ብር ዋስትና ከእስር እንዲወጡ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም አሁንም ተሰውረዋል ተባለ!

የባልደራስ ለእውነተኛና ዲሞክራሲ ፓርቲ የአደረጃጀት ዘረፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ፍ/ቤቱ ለመጨረሻ ጊዜ በ400 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም እስካሁን አልፈቱም ። አሁንም እንደቸሰወሩ ባለቤታቸው ተናገሩ።

ባለቤቱ እንደሚሉት ከሆነ በዚህ ሰዓት ከወረዳ 9 ፓሊስ ጣቢያ ጠዋት ወደ አልታወቀ ቦታ እንደወሰዱት መረጃ ደረሶኝ ነበር። ነገር ግን ቀን ከሌሊት እየተሰቃየን ባለንበት ሰዓት ቀደም ብሎ የታሰረበት እስር ቤት ሂደን ስንጠይቅ ለቱሪስት ነዉ እኛ ጋ ያመጡት እንጂ በወንጀል አይደለም። አሁን ግን ከዚህ የለም በማለት የፀጥታ አካላት የነገሩን ሲሆን የት እደወሰዱት ንገሩን ስንላቸቸዉ አዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ነዉ የወሰዱት የሚል ምላሽ ሰጠውናል።

ያልታወቀ ስልክ ደዉለዉ ስንታየሁ ነኝ በማለት ያልሆነዉን በማስመሰል አወራኝ። የባለቤቴን ድምፅ ጠንቅቄ አዉቃለሁ አንተ ስንቴ አይደለህም አልኩት ትላለች ወ/ሮ ውዴ ስንቄ። የደወለው ማንነቱን የማላውቀው ግለሰብ ለማንም ሰዉ እንዳትናገሪ ወደ ኦሮሚያ ክልል ወስደነዋል በማለት በቁጣ በስልክ ደውሎ ነገረኝ ትላለች የአቶ የስንታየሁ ቸኮል ባለቤት።