በጉራጌ ዞን በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ ውይይት ማካሄድ ተከለከለ

በጉራጌ ዞን በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ተከለከለ።

በተጨማሪ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ተጥሏል።

ውሳኔው የተላለፈው በዞኑ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ ስብሰባውን ካካሄደ በኃላ መሆኑን ከወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያወጣው መረጃ ያሳያል።

በዚህም ኮማንድ ፖስቱ ፦

– ከዛሬ ነሀሴ 12 ጀምጎ በዞኑ በማንኛውም ቦታ ማንኛውም አይነት መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ስብሰባ፣ ውይይት ማካሄድ ከልክሏል።

– በመንግሥት የስራ ሰአት የቢሮ ሀላፊም ይሁን ባለሙያ በቢሮ አለመገኘት እንደማይችል አሳስቧል።

– የንግድ ሱቆችና ተቋማትን ያለምንም ምክንያት መዝጋትም ከልክሏል።

– ማንኛውም ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ከልክሏል።

– የሞተር ሳይክል እንቅክቃሴ እስከ ምሽት 1 ሰአት ብቻ እንዲሁም የባጃጅ እንቅስቃሴ እስከ ምሽት 2 ሰአት ድረስ ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ አዟል።

ኮማንድ ፖስቱ የተላለፉትን ትእዛዛት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በወልቂጤ ከተማ ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ የሰፈረው መረጃ ያሳያል።