“ገበያኑ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተለቀቀ።
ሰለሞን ከእስር የተለቀቀው፤ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ አርብ ሰኔ 10 ቀን 2014 ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ነው።
ሰለሞን ዛሬ አምስት ሰዓት ተኩል ገደማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ ከሚገኘው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወጥቶ ከቤተሰቦቹ ጋር መቀላቀሉን እህቱ ትግስት ሹምዬ መናገሯን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።
ግንቦት 12 ቀን 2014 በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋለው ሰለሞን፤ ያለፉትን 28 ቀናት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በእስር ላይ አሳልፏል።
በተያያዘ ዜናም ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በ10 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል።