በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይሆን?

ላለፉት 17 ወራት በጦርነት ሲናጥ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢ የትግራይ ኃይሎች ከአፋር ወጥተናል ማለታቸውን ተከትሎ መረጋጋት ያሳየ ቢመስልም ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ዳግም ግጭቶች ሊያገርሹ እንደሚችሉ እየታዩ ነው። የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑት አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከፍተው ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱን ቢቢሲ ከምንጮቹ አረጋግጧል።…