አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር እልህ ተጋብታለች፤ 7 የአዲስ አበባ ቅርሶችን እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ሰጠች ።

አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጋር እልህ ተጋብታለች፤ 7 የአዲስ አበባ ቅርሶችን እንዲፈርሱ ትዕዛዝ ሰጠች ። ማፍረሱን ከፕላን ኮሚሽን ጋር አገናኝቶታል። የፕላን ኮሚሽን እዚህ ውስጥ በምን አውድ እንደገባ የሚታወቅ ነገር የለም።
  • አንበሳ መድሃኒት ቤትን ጨምሮ 7 የአዲስ አበባ ቅርሶችን እንደሚያፈርስ መስተዳድሩ አስታወቀ
No photo description available.በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ሰባት በቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ሊፈርሱ መሆኑ ተገለፀ። ቅርሶቹ የሚፈርሱት የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት አስተዳድር ቢሮ “ቦታው ለልማት እፈልገዋለሁ” በማለቱ እንደሆነ ሸገር ኤፍ ኤም ራዲዮ ጣቢያ ዛሬ ዘግቧል።
በፈረሳ እቅዱ ከተካተቱት መካከል ታሪካዊው አንበሳ ፋርማሲ፣ የራስ ናደው አባ ወሎ ቤት፣ የተክለ ማርያም ባሻ ቤት፣ የደጃዝማች ሊበን ቤት፣ የቀድሞው አድዋ ሆቴል እና ከጣይቱ ሆቴል ጋር የተያያዙ ቤቶች ይገኙበታል። እነኝህ ቤቶች የአዲስ አበባን አመሰራረት የሚያሳዩ ታሪካዊ ቤቶች ናቸው። በቅርስነት ከመመዝገባቸውም በተጨማሪ አዲስ አበባ በምትመራበት ማስተር ፕላን የተካተቱ ናቸው።
ሆኖም፣ የመሬት አስተዳድር ቢሮ “በቅርስነት ስለመመዝገባቸው ከፕላን ኮሚሽን ማስረጃ ካልመጣልኝ አፈርሳለሁ” ብሏል። የፕላን ኮሚሽን እዚህ ውስጥ በምን አውድ እንደገባ የሚታወቅ ነገር የለም።
ጉዳዩን ባልደራስ እንደሚከታተለውም ፓርቲው አስታውቋል ።
ከአራዳ ክ/ከተማ የወጣ ሰነድ እንደሚነግረን በ2013 ዓም ዳግም ምዝገባ በታሪካዊ ቅርስነት የተመዘገቡ ቤቶች ዝርዝር ውስጥ ምልክት የተደረገባቸው ቤቶች በአዳነች አበቤ ትህዛዝ የአዲስ አበባን ጥንታዊ ቅርሶች በአጭር ጊዜ እንዲፈርሱ መመሪያ የተሰጠባቸው ናቸው።
አንበሳ ፋርማሲ ኒው አዲስ (ሰይጣን ቤት) እንዲሁም ሰርቢያ ኢምባሲ ከሒልተን ጀርባ ወደ ካሳንቺስ መሄጃ ከዘመን ባንክ አጠገብ የሚገኝ ሕንፃ ነው እነዚህ ቤቶች በጥንታዊነታቸው በቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን የተመዘገቡ መሆኑ ይታወቃል። የአዲስ አበባን አሻራ የማጥፋት እኩይ ተልዕኮ በኦህዴድ/ብልፅግና መነፅር ይህን ይመስላል።