ትላንት ከአዲስ አበባ የተባረሩት ተፈናቃዮች፣ በደብረ-ብርሃን ተቀባይ አጥተው ወደ አርሲ ጉዞ ላይ ናቸው

ትላንት ከአዲስ አበባ የተባረሩት ተፈናቃዮች፣ በደብረ-ብርሃን ተቀባይ አጥተው ወደ አርሲ ጉዞ ላይ ናቸው

ትላንት ያለ ፍቃዳቸው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ-ብርሃን የተላኩት የወለጋ ተፈናቃዮች፣ ደብረብርሃን ሲደርሱ “ ካምፑ ሞልቷል፤ እንደምትመጡም አልተነገረንም፣ አንቀበልም ” ከተባሉ በኋላ የጫኗቸው መኪኖች ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ እንዲመለሱ ተደርጎ፣ በሸኖ ከተማ መኪና ላይ አድረዋል፡፡

ዛሬ ሳይነጋጋ ወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ ጉዞ የጀመሩት ተፈናቃዮቹ፣ በአሁኑ ሰዓት ቱሉ ዲምቱ ኮንዲሚኒየም የደረሱ ሲሆን፣ “ ወደ አሩሲ ትሄዳላችሁ፣ ወደ አዲስ አበባ መግባት አትችሉም ” ተብለዋል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ፣ ተፈናቃዮቹ ወደ አሩሲ አንሄድም “ በማለታቸው ውዝግብ ተነስቶ፣ በፖሊስ ተከበው መኪኖቹ ወደ አሩሲ መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡

Balderas ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ