አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በዓል ሲያከብሩ የነበሩ ኦርቶዶክሳዊያንን አስገደለ

በደም የሰከረው አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በዓል ሲያከብሩ የነበሩ ኦርቶዶክሳዊያንን አስገደለ

ለዝግጅት ክፍላችን በደረሰን መረጃ መሠረት በዛሬው ዕለት ታቦተ ማርያምና ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንበራቸው ወደ ወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ ጽንፈኛው የእነ ሙጃብ አሚኖ ቄሮና የኦሮሚያ ፖሊስ ስለተከለከሉ ጉዳዩን እዳኛለው ብሎ የመጣው የፌዴራል ፖሊስ፣ የሪፐብሊካን ጋርድና የአዲስ አበባ ፖሊስ መንገድ ዘግተው ታቦት አናሳልፍም ያሉትን ወንጀሎች ተተው በምስጋና፣ በዝማሬ፣ በማኅሌት ሲደክሙ የከረሙትን ካህናት፣ ዲያቆናት፣ የሰንበት ተማሪዎችና ምዕመናን ላይ ጥይት ሲያርከፈክፉ አምሽተዋል። ህጻናት ተጎድተዋል፣ በርካታ ምዕመናን በጥይት ተመተዋል። ቆስለው ሀኪም ቤት የገቡም ብዙ ናቸው።ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እናሳውቃለን። በድረገጽ የተለቀቀ ቪዲዮ ተመልከቱ።