ከ500 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በኦነግ ሸኔ ከ400ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከኦሮሚያ ተፈናቅለዋል ፤ ይህ ቁጥር መንግስት ያመነው ነው።

DW ፤ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ጢቂት ጊዜያት ብቻ ከ500 ሺህ በላይ ነዋሪዎች በታጣቂዎች ጥቃት ከንብረት ቀዬያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ የክልሉ ቆላማ አከባቢዎች ዘንድሮ በተከሰተው ድርቅ ከ400 ሺህ በላይ ዜጎች ለችግር መዳረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የክልሉ መንግሥት ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ግብርና ላይ አተኩሮ እየሰራ መሆኑን ነው ያመለከቱት፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ዛሬ የክልሉ የልማትና ሰላም እንቅስቃሴ በሚል ርዕስ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት፤ እንደ አገርም ሆነ በክልሉ ተጋርጦ የቆየውን የፀጥታ ችግሮችን ከመቋቋም ጎን ለጎን የልማት ስራዎች ላይም በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ነው ያመለከቱት፡፡ በዚህም በአገሪቱ ከፍተኛ ምርት ከሚሰበሰብበት ከክልሉ ባለፈው ዓመት በመኸር ምርት ከታረሰው 6.3 ሚሊየን ሄክታር በ5.8ቱ ላይ የተዘራውን መሰብሰብ መቻሉን ጠቅሰዋል፡፡ አሁን ላይ እየተሰራበት ያለው የመስኖ ስንዴ ልማትና ምርታማነትን ያሳድጋል የተባለው የተፋሰስ ስራ መሆኑን በማከል፡፡

Äthiopien Hailu Adugna, Pressesprecher der Oromia Region በሌላ በኩል ሰፊ የፀጥታ መደፍረሶች ተስተውሎበት ዓመቱን በሙሉ በቀጠለው በኦሮሚያ ክልል የዜጎችን ሰላምና ፀጥታ ሲስተጓጎል ተስተውሏል፡፡ መንግስት ፀጥታውን በማደፍረስ የሚከሰው ሸነ በሚል ስም የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ጦር በሚንቀሳቀስባቸው የወለጋ አራቱ ዞኖች፣ በምዕራብና ሰሜን ሸዋ እንዲሁም በሁለቱ የጉጂ ዞኖች እንቅስቃሴውን ለመግታት ሶስት አበይት ተግባራት በመንግስት መከናወኑንም አውስተዋል አቶ ኃይሉ፡፡

በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ምስራቅና ምዕራብ ሃራርጌ ቆላማ ስፍራዎችን ጨምሮ በአራት ዞኖች ባጋጠመው የድርቅ አደጋ ከ400 ሺህ በላይ ዜጎች ለችግር መዳረጋቸውን ያመለከተው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ሃላፋ መግለጫ፤ በሰውና እንስሳት ላይ የህይወት አደጋ እንዳይደርስ ምላሽ እየተሰጠ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ አፕ…

በሌላ በኩል በክልሉ በሚንቀሳቀሰው ታጣቂ ቡድን ምክኒያት ብቻ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡

በአገሪቱ የታሰበው የብሔራዊ ምክክር ላይ እንዲሳተፉ ታስቦ በቅርቡ ስለተለቀቁት ፖለቲከኞችም የተጠየቁት አቶ ኃይሉ መልስ ሰጥተዋል።

በኦሮሚያ ታጣቂዎችን ለመምታት በሚወሰደው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ይፈጸማል የሚባለውን መረጃ ግን አቶ ኃይሉ አጣጥለውት በኦሮሚያ ምንም አይነት የአየር ጥቃት አለመፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ አቶ ሃይሉ በኦሮሚያ በተለይም በምስራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች አካባቢ ከኦሮሞ ነጻነት ጦር በተጨማሪ የጉሙዝና አማርኛ ተናጋሪ ያሏቸው ታጣቂዎችም ህብረተሰቡን እንደሚያፈናቅሉና በሁሉም ላይ መንግስት ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስድም ነው በመግለጫቸው የጠቀሱት