የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩዎች መጠቆሚያ ጊዜ እንዲራዘም ተጠየቀ

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩዎች መጠቆሚያ ጊዜ እንዲራዘም ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የዕጩዎች መጠቆሚያ ጊዜ እንዲራዘም ጠየቀ፡፡ ፓርቲው ማክሰኞ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው በቂ የሕዝብ ምክክር ሳይደረግበት መሆኑን ገልጿል፡፡