የነ ስብሃት ነጋ መፈታት በሚኒስትሮች ምክርቤትም ሆነ በተወካዮች ምክር ቤትም አልተወሰነም

የኢዜማ ብሄራዊ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ በፊስቡክ ገፃቸው የነስብሃት ነጋ መለቀቅ አስመልክተው የሚከተለውን አስፍረዋል።

በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የክስ መዝገብ የተጠቀሱትን አቶ ስብሃት ነጋ እና የተወሰኑ ሰዎች መፈታታቸውን በተመለከተ በኢዜማ ብሄራዊ ስራ አስፈፃሚ የአስቸኳይ ስብሰባ ላይ የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መጀመሪያ የተጠየቁት በሚንስትሮች ም/ቤት ጉዳዩ ቀርቦ እንደሆነ መረጃ እንዲሰጡ ነው ።
በሰጡት መልስ ጉዳዩ በሚንስተሮች ም/ቤት እንዳልቀረበ እና እንደ ማንኛችንም በሚድያ እንደሰሙ ነው ።
ለነገሩ ጠ/ሚንስትሩም ይህን (እሳቸውም እንዳልሰሙ) አረጋግጠዋል (የጉድ ሀገር!) የኢዜማም መግለጫ የሚጠቁመው አቋሙን ነው ።
ከዚህ እውነት በወጣ መልኩ ኢዜማ ላይ ማላዘንና ሴራ መጎንጎን ትርጉም አልባ ነው ። የሚገኝ ጥቅምም የለውም ።