በቡኖ በደሌ ተፈናቅለው በሽማግሌዎች ማግባባት የተመለሱ እንደገና ቤታቸው ተቃጠለ

መረጃ ቲቪን ሰብስክራይብ በማድረግ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ ትንተናዎችን፣ የኪነጥበብ ፕሮግራሞችን እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

 

በኦሮሞ ክልል የክልሉ ፖሊስ ሃላፊዎች ከሕግ በላይ በሆኑ አካላት በተለይም በኦሮሞ ክልል በሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰባት ላይ የሚደርሰውን  መከራና እንግልት ማስቆም አለመቻል ብቻ ሳይሆን፣ የሚፈጸሙ በደሎችንም ለሕዝብ ያቀርባሉ ብለው የሚያስቧቸውን በማሳደድ ላይ እንደተጠመዱ ጋዜጣኛ ጌታቸው ሽፈራው ዘገበ።

በኢሊባቡር፣ የኦሮሞን ማህበረሰብ በማይወክሉ ጥቂት አክራሪዎችና ጽንፈኞች “መጤ” ተብለው ብዙ ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ከቃያቸው መፈናቀላቸውንና መገደላቸውን በስፋት መዘገቡ ይታወሳል።  ድርጊቱ ከኦሮሞ የአቃፊ ባህል ያፈነገጠ እንደመሆኑ፣ ሽማጋሌዎች  የተገደሉትን ባያተርፉም፣ ብዙ የተፈናቀሉትን እንዲመለሱ ባያደረጉም፣ የተወሰኑትን ግን አግባብተው ወደ ቅያቸው እንዲመለሱ አድርገው ነበር።

ሆኖም ግን በሽማግሌዎች ማግባባት የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ላይ አሁን ጥቃትና በደለ እየተፈጸመ መሆኑ እየተሰማ ነው። “ኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ደዴሣ ወረዳ በርካታ አማራዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበር ቢሆንም “ሽማግሌዎች ወደ ቤታችሁ ተመለሱ” ብለዋቸው ተመልሰው ነበር”  ብሎ  የዘገበው ጋዜጠኛ ጌታቸው፣   ሽማግሌዎች የሰሩትን በጎ ስራ እንደገና በመሻር ጽንፈኞችና አክራሪዎች  እንደገናጥቃት መፈጸማቸው አስፍሯል።

” በ25/2/2011 ዓም ቡረቃ ጃለላ ቀበሌ 7 የአማራ ቤቶች ተቃጥለዋል። ተፈናቃዮቹ “ተመለሱ” ተብለው ወደቀያቸው ከተመለሱ በኋላም የአካባቢው ባለስልጣናት እና ታጣቂዎች በሕዝብ ላይ በደል እየፈፀሙ መሆኑ ተገልፆአል። አማራዎችን ከቀያቸው በማፈናቀል የኦዴፓ (ኦህዴድ) ባለስልጣናትና የክልሉ መንግስት መዋቅር ተሳታፊ ነው ተብሏል” ሲልም  ጽንፈኞችና አካራሪ ቡድኖቹ ራሳቸው በኦዴፓ/(ኦህዴድ) መዋቅር ውስጥ ያሉ  የአካባቢው ባለስልጣናታ ታጣቂዎች እንደሆኑም ነው ጋዜጠኛ ሽፈራው የጦመረው።

ጋዜጠኛ ጌታቸው ጽሁፉን ሲያጠቃላል ” የቀበሌ ባለስልጣናት በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል ለሚዲያ ያደርሳሉ ብለው የጠረጠሯቸውን ግለሰቦች በማሳደድ ላይ መሆናቸውን ተገልፆአል። በሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል ታጋልጣለህ የተባለ ግለሰብ ለሕይወቱ ስለሚሰጋ ተደብቆ እንደሚኖር ገልፆልኛል” ሲል በአካባቢው የሚፈጸውም ግፍና በደል ለማፈን ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ነው ለማሳየት የሞከረው።