በባቲ – በጋሸና – በሸዋ ደብረሲና የወገን ኃይል ከባድ ፍልሚያ እያደረገ ነው

በሶስት ግንባር ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ::
በባቲ – በጋሸና እና በሸዋ ደብረሲና የወገን ኃይል ከባድ ፍልሚያ እያደረገ ነው ::
በአሁኑ ሰዓት ወጣሙ ወያኔ ከደብረሲና እየተገፋ ሲሆን በባቲ ግንባር መከላከያ ሲቀርበው ከማፈግፈግ ውጭ ሌላ አማራጭ አላገኘም ::
በጋሸና ግንባር ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጠላቱን ሳይቀብር ላይመለስ ሲነሳ በላሊበላ ግንባር ሰኞ ገበያ ላይ ልዩ ኃይሉና የላስታ ፋኖ በፍፁም ቁርጠኝነት እየተዋጋ ነው ::
ቆቦን ጨምሮ በወርቄና በሶዶማ እንዲሁም በመካነ ሠላም ሽምቅ ተዋጊው የወያኔን ሎጅስቲክ መንገድ እየጠበቀ እያወደመ የስንቅ ግብዓቱን በማሳጣት የአሸባሪውን ቡድን መቀመቅ ውስጥ እየከተተ ነው ::