የኢትዮጵያ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል የሲኤንኤን ዘገባ በመቃወም ግምገማና የሕግ ምርመራ እንዲደረግበት ይጠይቃል ተባለ

The Ethiopian American Civic Council

የኢትዮጵያ መንግስት ባለሥልጣናት በትግራይ ተወላጆች ላይ የዘር ማጽዳት ድርጊቶችን ፈጽመዋል በሚል ሲኤንኤን ያስተላለፈው ዘገባ ራሱን የቻለ ግምገማና የሕግ ምርመራ እንዲደረግለት የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል ጥሪ እያቀረበ ነው። አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንን መዘዝ እና ብዙ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን ፍርሃት አቅልለው ማየት የለባቸውም ያለው መግለጫው ካውንስሉ ለሲኤንኤን ኦፊሴላዊ ደብዳቤ መላኩን ጠቁሞ የካውንስሉን የበላይ ዮሴፍ ተፈሪን ጠቅሶእንዳለው ዘገባው የማያስተማምንና ምንም ማረጋገጫ የሌለው ግምታዊ ነው ብሏል። በዘገባው በሱዳን ተገኙ የተባሉት አስከሬኖች እውነታውን የሚያረጋግጥ የፎረንሲክ ባለሙያዎች ስም ዝርዝርም ይሁን በቂ አሳማኝ ማስረጃዎች ባልተዘረዘሩበትየሕግ ባለሙያዎች ያላረጋገጡት ስለሆነ የሕግ ምርመራ እንዲደረግስራ መጀመሩ ታውቋል።

የኢትዮጵያ አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል እና አድቮከሲ ኔትወርክ ሰሞኑን CNN የተባለው ሚዲያ ያወጣውን የሀሰት ዘገባ በመቃወም በመላ አለም ለሚገኙ ጋዜጦች ዘገባው እውነትን ያላማከለ እንዴውም በዘገባው ላይ የህወሃት አባል የሆነን ሰው በማቅረብ የጋዜጠኝነት ሙያን አንድ የሽብርተኛ ቡድን ለማገዝ ሲባል አራክሰዉታል ሲል ተቃውሞውን አሰምቶል። በዚህም ዝም ሳይል ይቅርታ ካልጠየቀ ካውንስሉ ያገኘውን መረጃ ይዞ በህግ አግባብ የሚጠይቅ መሆኑን አስስቧል።

ካውንስሉ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ያገኙታል።

https://miniliksalsawi.medium.com/ethiopian-diaspora-calls-for-independent-review-of-cnn-report-bbdb769a75b6