ጠ/ሚ ዐቢይ አሁን ባለው የትግራይ ግጭትና አመጣዋለሁ ካሉት ለውጥም ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ባለመጠበቃቸው እየተተቹ ይገኛሉ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አከናውናቸዋለሁ ብለው የነበሩ ተግባራት ሲገመገሙ – BBC Amharic

ከሦስት ዓመታት በፊት ወደ ስልጣን የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጎረቤት አገር ኤርትራ ጋር ሰላም በማስፈን እንዲሁም በጭቆና በምትታወቀው አገር ላይ የፖለቲካ ምኅዳሩን በማስፋትና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በማምጣት ከፍተኛ ምስጋና ተችሯቸው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድሰላም በሌለበት ሁኔታ ለብዙ ዓመታት ተፋጠው በነበሩት ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የድንበር ግጭቱን የመቋጨት ጥረታቸው ከሁለት ዓመት በፊት የኖቤል ሽልማት አሸናፊ አድርጓቸዋል።

ነገር ግን አሁን ባለው የትግራይ ግጭትና አመጣዋለሁ ካሉት ለውጥም ጋር በተያያዘ ቃላቸውን ባለመጠበቃቸው እየተተቹ ይገኛሉ።

ሁለት ሳምንታት ያህል በቀረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫም ለመጀመሪያ ጊዜ ብበልፅግና ስም ይወዳደራሉ።

በባለፉት ዓመታት አድርገዋቸው የነበሩ ዘመቻዎችንና የገቡዋቸውን ቃሎች መለስ ብለን እንቃኝ።

“45 ሺህ ያል እስረኞች ተለቀዋል”

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎችን በማሰር ከፍተኛ ወቀሳዎች ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይደርሱት ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የፖለቲካ እስረኞችን በመልቀቅ ተወድሰዋል።

በሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዓለም አቀፍ ድርጅት አምነስቲ ተመራማሪ የሆኑት አቶ ፍስሐ ተክሌ በወቅቱ የተለቀቁ እስረኞች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም አስከ 45 ሺህ እንደሚደርስ ተናግረዋል።

ነገር ግን በባለፉት ዓመታት በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።

በርካታ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶችም ሪፖርት የሚያደረጉት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ነው።

“አምነስቲ በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ከሁለት ዓመት በፊት በጥር ወር በሰበሰባቸው መረጃ መሰረት 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸውንና ይህም ሁኔታ ከወራት በኋላ መቀጠሉን ነው” ይላል የአምነስቲ ሪፖርት።

“በተመሳሳይ መልኩ በሰንቃሌ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከል 2 ሺህ የሚሆኑ እስረኞች መታሰራቸውን የቀድሞ ታራሚዎች ተናግረዋል” ብሏል።

ከዓመት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርት እንዳደረገው የታዋቂው ሙዚቀኛ የሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተነሳው ቀውስ 9 ሺህ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል።

“በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መምጣት በፊት በነበሩት ወራት እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመጡ በመጀመሪያ ወራት መለቀቅ አስደናቂ ነበር። ነገር ግን ይህ ለአጭር ጊዜ ነው አልቆየም” በማለት በሰብዓዊ መብቶች ላይ የሚሰራው ሂውማን ራይትስ ዋች ላቲሻ ባደር ተናግረዋል።

“በአማራ ክልል ከደረሰው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ጋር ተያይዞ መንግሥት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ታስረዋል። ይህም በዚያው ሁኔታ ቀጥሎ በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ በርካታ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶችና ሌሎች ግለሰቦች ታስረዋል።”

ግድቡ ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ አድርጓታል”

የአባይ ወንዝ ኢትዮጵያንና ሱዳንን በሰሜን ምዕራብ ድንበር በኩል ያገናኛቸዋል። በወንዙ ላይ ደግሞ አገራቱን እያወዛገበ ያለው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለግንኙነቶች ዋነኛ ማዕከል ሆኗል።

ኢትዮጵያ ግድቡ ሕዝቤን ከጨለማ የማወጣበት ለአገሪቱም ልማት የሃይድሮ ኤሌክትሪክ በማመንጨት ቁልፍ መሰረት ነው ትላለች።

ነገር ግን ግድቡ አገራቱ የሚወዛገቡበት እንዲሁም ውጥረቶች በከፍተኛ ሁኔታ የተጋጋሉበት እንዲሆን አድርጎታል በተለይም ከግብጽ ጋር።

ግድቡ የታችኛውን ተፋሰስ አገራት ጥቅም አይጎዳም የምትለው ኢትዮጵያ፤ በተደጋጋሚ ጠቃሚ ይሆናል ተብሎ የሚጠቀሰውም ሱዳንን በከፍተኛ ሁኔታ በጎርፍ ከመጥለቅለቅ ይታደጋታል የሚል ነው።

ነገር ግን ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ ከነበረው የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተከትሎ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ጎርፍ ተፈጥሯል።

“በሱዳን የነበረው ጎርፍ የተፈጠረው ከነሀሴ እስከ መስከረም በነበረው ወቅት ነው ። በዚያን ወቅት የህዳሴ ግድቡ በወንዙ ፍሰትም ላይም ሆነ በሱዳነ በነበረው ጎርፍ ጣልቃ አልነበረውም” በማለት በማንችስተር ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት መሃመድ ባሽር ይናገራሉ።

የውሃው ሙሌት ሲከናወን በሱዳንም የነበረው የውሃ መጠን ወርዶ የነበረ ቢሆንም ግድቡ ሲሞላ ግን ወንዙ ወደነበረበት ስፍራ ተመለሰ።

ሱዳን በአጠቃላይ የፕሮጀክቱ ደጋፊ ብትሆንም የህዳሴ ግድብ በሱዳን ጎርፍ ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተፅእኖ ከግድቡ አጠቃላይ አስራር ጋር እንዲሁም ከሱዳን ጋር ካለ ትብብር ጋር የሚያያዝ ይሆናል” ብለዋል ባሽር።

በ4 ዓመታት 20 ቢሊዮን ችግኞች እንተክላለን

‘ግሪን ሌጋሲ’ የተሰኘው መርሃ ግብር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ከሶስት ዓመታት በፊት የገቡት ቃል በሶስት ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ 5 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል ይጠይቃል።

ከሁለት ዓመት በፊት ከሰኔ እስከ መስከረም ባለው የክረምት ወቅት መንግሥት አራት ቢሊዮን ችግኞች በሃገር አቀፍ ደረጃ ተተክለዋል ብሏል። በአንድ ቀን 353 ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል የሚለውን ዜና ጨምሮ።

ባለፈው ዓመት ደግሞ አምስት ቢሊዮን ተተክሏል የተባለ ሲሆን በዚህ ዓመት ስድስት ቢሊዮን እንሚተከል ተነግሯል። እንደ መንግሥት ከሆነ ዕቅዱ እንዲሳካ በሚቀጥለው ዓመት አምስት ሚሊዮን ችግኞች መተከል አለባቸው።

ይህ የመንግሥት ዕቅድ በጣም ሰፊ ሲሆን ለማጣራት እጅግ ከባድ ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የችግኝ ተከላ ወቅት የቢቢሲ ሪያሊቲ ቼክ የተባለው ቁጥር ያህል ችግኝ ተተክሏል የሚለውን ለማጣራት ያደረገው ምርመራ በቂ ማስረጃ ለማግኘት እግጅ አዳጋች ነው።

ስለ ችግኝ ተከላው ያለ ብቸኛ መረጃ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተገኘ ሲሆን ይህን ቁጥር ገለልተኛ በሆነ መንገድ ማጣራት ቀላል አይደለም።

ሌላው መጣራት ያለበት ጉዳይ ምን ያክሉ ችግኞች ፀድቀዋል የሚለው ነው።

ባለሙያዎች ከተተከሉት ችግኞች 30 በመቶው ብቻ እንደፀደቁ ይገምታሉ። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ችግኞች 84 በመቶ የመፅደቅ ዕድል አላቸው ይላሉ።

የችግኝ ተከላ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

“የቴሌኮም ዘርፍን ለገበያ ክፍት እናደርጋለን”

የኢትዮጵያ የቴሌኮም ሽያጭ በኢትዮጵያ መንግሥት “የምዕተ ዓመቱ ምርጥ ሽያጭ” ቢባልም ከተያዘለት ጊዜ የዘገየ ነበር።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሐመድ መንግሥት የቴሌኮም ዘርፉን ነፃ እንደሚያደርግ ቃል የገባው ከሶስት ዓመት በፊት ነበር።

በመንግሥት የተያዘው ኢትዮ-ቴሌኮም ጠቅላላውን የቴሌኮም ዘርፍ በብቸኝነት ተቆጣጥሮት ቆይቷል። ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገንዘብና ልምድ እጥረትን ጨምሮ በርካታ ችግሮች አሉበት ብለዋል።

የመንግሥት ዕቅድ ሁለት የቴሌኮም ፈቃዶችን ለአዳዲስ ኔትወርክ አቅራቢዎች መሸጥና ከኢትዮ-ቴሌኮም ደግሞ አክሲዮን መሸጥ ነበር።

ቢሆንም ባለፈው ሚያዚያ ወጥቶ የነበረው የኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜ አልፏል።

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ባለስልጣን አርማ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ግንቦት ላይ ደግሞ ኤምቲኤን ያቀረበው የቴሌኮም ፈቃድ ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል። ነገር ግን ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበው ጥያቄ ግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በሚል ስም ፈቃድ አግኝቷል።

በገንዘብ ሚኒስቴር ነባር አማካሪ የሆኑት ብሩክ ታዬ መዘግየቱ የመጣው የቴልኮም ዘርፉን ነፃ ማድረግ አዳዲስና ረቂቅ ሕጎች ስለሚጠይቅ ነው ሲሉ ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሌላው በመንግሥት የተያዘውና በነፃ ገበያው ለሽያጭ እንደሚቀርብ የተነገረለት ኢትዮጵያን ኤርላይንስ ነበር። ነገር ግን ባለፈው ዓመት መንግሥት ሀሳቡን ቀይሯል።.