የታቀደዉ ምርጫ የእስካሁን ሒደትና ዝግጅት የምርጫን ዝቅተኛ መስፈርት እንደማያሟላ ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


DW : በመጪዉ ሰኔ 14 አዲስ አበባ ዉስጥ ሊደረግ የታቀደዉ ምርጫ የእስካሁን ሒደትና ዝግጅት የምርጫን ዝቅተኛ መስፈርት እንደማያሟላ ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ።ፓርቲዉ በርዕሠ-ከተማይቱ 10 ክፍለ ከተሞች አደረግሁ ያለዉ ጥናት ዉጤት፣ የቅድመ ምርጫ ሂደቱ “አስገዳጅ፣ ዝቅተኛ ፣ የነፃነት ፣ የፍትኃዊነትና የዴሞክራዲያዊነት መርህን ያላሟላ” ብሎታል።ፓርቲዉ በምርጫዉ ለመካፈል እስር ቤት የሚገኙ መሪዎችን ጨምሮ በእጩነት አቅርቧል። ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ጥናቱ ግን በመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም ኢ ፍትኃዊነት ጎልቶ መታየቱን፣ በዕጩዎች፣ በመራጮች እና አባላት ላይ ግድያ፣ እሥር፣ ማዋከብና የደኅንነት ሥጋት መኖሩን አመልክቷል።