በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ ናቸው – የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸው ተናገሩ፡፡

ዋና ጸሃፊው የትግራይ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እጅግ አስከፊ ወደ ሆነ ደረጃ መሸጋገሩ አይቀሬ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የተጋረጠውን የረሃብ አደጋ ለመግታት ሰብአዊ እርዳታ ማዳረስ እንዲሁም በቂ ፈንድ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ዋና ጸሃፊው በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክት አስታውቋል፡፡

“አሁን የሚከናወኑ ተግባራት ለበርካታ ሰዎች የመኖርና አለመኖር ጉዳይ መሆናቸውን መረዳት ተገቢ ነው”ም ነው ያሉት የተ.መ.ድ ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፡፡

የጉተሬዝ ትግራይን የተመለከተ መግለጫ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ያሉ የግጭቱ ተዋናዮች ተኩስ እንዲያቆሙና ያልተገደበ የስብአዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ጥሪ እያደረገ ባለበት ወቅት መሆኑን አል ኣይን በድረገፁ አስነብቧል።

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ/ኦቻ/ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሳቢያ በትግራይ ያለው የሰብዓዊ ቀውስ አሳሳቢ መሆኑን እና በኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ ወዲህ ከፍተኛ የረሀብ አደጋ እንዳንዣበበ ባለፈው ሳምንት አሳትውቋል።