የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የ2013 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ይፋ ሆነ፡፡

በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ለወንድ 380 ሲሆን ለሴት ደግሞ 368 መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለታዳጊ ክልሎችና አርብቶ አደር አካባቢዎች ደግሞ ለወንድ 368 እንዲሁም ለሴት 358 መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ዑርቃቶ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 350 እንዲሁም ለሴት 345 ሲሆን ለአርብቶ አደሮች አካባቢ ደግሞ 358 መግቢያ ውጤት ሆኗል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትግራይ እና መተከል ደግሞ ለወንድ 358 ለሴት ደግሞ 350 መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታው አስታውቀዋል፡፡

ለማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ለወንድ 370 ሲሆን ለሴት ደግሞ 358 ሆኗል፡፡

ለታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች ለወንድ 358 እንዲሁም ለሴት 348 ሆኗል፤ ለአካል ጉዳተኞች ለወንድ 340 እንዲሁም ለሴት 335 እንዲሆን ተወስኗል፡፡

በትግራይና መተከል ደግሞ ለወንድ 348 እንዲሁም ለሴት 340 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡