የኢትዮጵያ መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊና የፖለቲካ መብቶች ጥሰት ፈጽመዋል – የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ማክሰኞ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊና የፖለቲካ መብቶች ጥሰት ፈጽመዋል አለ።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ይፋ የተደረገው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና የፀጥታ ኃይሎች ሕጋዊ ያልሆነ ግድያ በተለያዩ አካባቢዎች ፈጽመዋል ያለ ሲሆን፣ ለዚህም የተለያዩ የውጭ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማትንና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቶችን ዋቢ አድርጓል።
ከተፈጸሙት ሕገወጥ ግድያዎች በተጨማሪ በሕግ የተከለከሉ የጭካኔና ማሰቃየት ተግባራት፣ እንዲሁም የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች በፀጥታ ኃይሎች በትግራይ ክልልና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መፈጸማቸውን በሪፖርቱ አመልክቷል።
ተጨማሪ ያንብቡ