የአማራና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል እየመከርን ነው አሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


May be an image of 1 person, sitting, standing and indoorየአማራ እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በሁለቱ ክልሎች የጋራ ሠላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ነዉ፡፡ በምክክር መድረኩ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል በትብብር መሥራት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
በሁለቱም ክልሎች የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት ማስቆም፣ የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ወገኖች ፍትሕ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀረቡ ማድረግ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም እንዲሁም በክልሎቹ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አኳያ በትብብር ለመሥራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ክልሎች አመራሮች በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ሕዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣ አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሠሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይቱ አንኳር ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ በመድረኩ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ እየመሩት ነዉ፡፡
May be an image of 2 people, people standing and people sitting