በሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

በሚያዚያ ወር ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ በሚያዚያ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 43 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ ሲሆን በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረበት ዋጋ የ5 ብር ከ5 ሳንቲም ጭማሪ እንዳለው አስታውቋል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ እንደሚችልም ሚኒስቴሩ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።