የአማራ ልዩ ኃይል ከሰባት መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀለብን – የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር


የመረጃ ቲቪን 24/7 የሳተላይት ስርጭት በመደገፍ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እና ትክክለኛ መረጃ በማግኘት እራሱን ከተጋረጠበት አደጋ መከላከል እንዲችል እናግዝ። በአሁኑ ወቅት ከመረጃ ቲቪ በስተቀር ሌሎች ሁሉም በኢትዮጵያ ያሉ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የመንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ናቸው። ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ የከፈትነው የመረጃ ቲቪ የሳተላይት ስርጭት የአንድ ዓመት ወጪን ለመሸፈን ነው። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን ድጋፍዎትን ይለግሱ » https://gofund.me/54405070

በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ከ7መቶ ሺህ በላይ ነዋሪዎች በአማራ ክልል የጸጥታ ኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ሲል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሙዩኒኬሽንስ ቢሮ ገለጸ። ይህ ሁኔታ በክልል ያለው ሰብዓዊ ቀውስ እንዲባባስ እንዳደረገ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ እቴነሽ ንጉሰ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል “ከምዕራብ ትግራይ ከሰባት መቶ ሺህ በላይ የትግራይ ተወላጅ ተፈናቅሏል” መባሉን የአማራ ክልላዊ መንግሥት አስተባብሏል።

“ይህንን ያህል ቁጥር ያለው የትግራይ ተወላጅ በአካባቢው አይኖርም” ብለዋል የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ለቪኦኤ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።