ሱዳን የኢትዮጵያ የጦር ጄት ድንበር ጣሰ አለች


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

ሱዳን፣ የኢትዮጵያ የጦር ጄት «የዓየር ክልሌን» ጥሶ ገባ በማለት ኢትዮጵያን ወቀሰች።አል ፋሻቅ በተባለዉ የድንባር ግዛት ሰበብ የሚወዛገቡት የሁለቱ ሐገራት ጠብ ሰሞኑን ተካርሯል።

የሱዳን ጦር ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ግዛቶች መያዙን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ትናንት አስታወቆ ነበር።የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀዉ ደግሞ የኢትዮጵያ የጦር ጄት ድንበር ተሻግሮ የሱዳንን የዓየር ክልል ጥሷል።

አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የጠቀሰዉ የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ እርምጃዉን «አደገኛና ምክንያት የለሽ» በማለት አስጠንቅቋልም።የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ግን ስለወቀሳዉ «ተጨባጭ መረጃ» የለኝም ማለታቸዉን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ጠቅሷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጦር መሣሪያ ጭኖ የነበረ አንድ የሱዳን ሄሊኮፕተር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ዛሬ ወድቆ ተከስክሷል።ሄሊኮፕተሩ የተከሰከሰው በአልገዳሪፍ ክፍለ ግዛት አል ሾዋክ ከተማ ከሚገኘው ከዋድ ዛይድ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ ነው።ሄሊኮፕተሩ እንደወደቀ በእሳት መያያዙም ተዘግቧል።የአደጋው መንስኤ በዉል አልተገለጸም። DW