የባልደራስ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ጨምሮ ከ20 በላይ ደጋፊዎች መታሰራቸው ታወቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

  • የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የተፋጠነ ፍትሕ መስጠት እንዲቻል ከቀጠሮ ቀን በፊት ችሎት ሰየመ።
  •  የፍርድ ቤት ውሎን ለመከታተል በስፍራው ከተገኙት የባልደራስ ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ጨምሮ ከ20 በላይ ደጋፊዎች መታሰራቸው ታወቀ
Image may contain: 1 personየባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፓርቲው ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ማሂን ጨምሮ ከ20 በላይ ደጋፊዎች መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ ያመልክታል::አክትቪስትና ጋዜጠኛ ሰብለወንጌል ታደሰና በርካታ ሰዎች በፖሊስ መታሰራቸውን ታወቀ::
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባላትን የፍርድ ቤት ውሎን ለመከታተል በስፍራው ከተገኙት በርካታ አዲስ አበቤያዊያን መካከል አክትቪስትና ጋዜጠኛ ሰብለወንጌል ታደሰ በስፍራው የትገኘች ሲሆን በፖሊስ ታፍሳ ባልቻ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ መታሰራቸው ተገልጿል::
“ወገናችን በመተከል እየታረደ ባለበት ወቅት እኛ የፍርድ ሂደት ለመከታተል በመገኘታችን ለእስር መዳረጋችን ለኛ ደህንነት እስርቤቱ ሳይሻል አይቀርም” ሲሉ እስረኞች መናገራቸውን ምንጮች አክለው ገልፀውልናል::
———————————–
በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የተፋጠነ ፍትሕ መስጠት እንዲቻል ከቀጠሮ ቀን በፊት ችሎት ተሰየመ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ የተፋጠነ ፍትሕ መስጠት እንዲቻል ከቀጠሮ ቀን በፊት ችሎት ሰየመ። የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር እስክንድር ነጋን ጨምሮ አምስት ተከሳሾች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
ተከሳሾቹ ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ በተከሰተው ግርግር እጃቸው አለበት በመባሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት። በዚህ የክስ መዝገብ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም፣ አስካለ ደምሴና በዋስትና የተለቀቁት ጌትነት በቀለ ይገኙበታል።ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ሲካሔድ የነበረውን ምርመራ ሲከታተል የቆየ ሲሆን የአቃቤ ሕግ ምስክር ለመስማት ለመጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ይሁንና ፍርድ ቤቱ ዛሬ እንዳስታወቀው የቀጠሮውን ቀን በማሳጠር ተከሳሾቹ ለዛሬ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲቀርቡ ያደረገው ችሎቱ በሶስት ቦታ ተከፋፍሎ እንዲሰራና የነበረበት ጫና እንዲቀንስ በመደረጉ ነው።ፍርድ ቤቱ የተፋጠነ ፍትሕ ለመስጠት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጾ የመጀመሪያውን የአቃቤ ሕግ ምስክር ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም መስማት እንደሚጀምር አሳውቋል።
ተከሳሾቹ በበኩላቸው ‘በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ እንድንችል አሁንም ምስክር ለመስማት የተያዘው የቀጠሮ ቀን ሊያጥር ይገባል’ ሲሉ ጠይቀዋል።ጉዳዩን የያዘው አቃቤ ሕግም ከምርጫ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ ነገር የለም፤ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ወር ቀጥሮት የነበረውን ጉዳይ ሰብሮ በአንድ ወር ለማየት መወሰኑ መልካም ነው ሲል ተከራክሯል።