“እስክንድር ነጋ ይፈታ” freeeskindernega.org በትዊተር ላይ @FreeEskinderN እና Instagram ላይ @freeeskindernega

“እስክንድር ነጋ ይፈታ” ዓለም አቀፍ ዘመቻ freeeskindernega.org በትዊተር ላይ @FreeEskinderN እና
Instagram ላይ @freeeskindernega 
ከሁለት ዓመት በፊት በንዴት የተበሳጨው ተረኛው አብይ አህመድ በአዲስ አበባና በኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥሪ በማድረጋቸው ብቻ በሰላማዊው እስክንድር ነጋና ባልደራስ ላይ ጦርነት እናካሂዳለን ሲል ደንፍቷል። በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ መቆጣጠር ስላልቻለ እያለከለከ አቅራርቷል። ከታሪክ አለመማር ነው እንጅ እነ ስብሃት ነጋም ህዝብ ላይ ሲሳለቁ፣ ሲያቅራሩና ሲያናፉ ነበር የኖሩት። “እግዚአብሔር እውነትን ያያል፣ ግን አይቸኩልም እንደሚባለው” ስብሀት ነጋና ባልደረቦቹ  ጊዜያቸው ሲደርስ ከቤተ መንግስት ተወግደው ወደ መደበቂያ ጉሮኖ ወርደዋል። አብይ አህመድም ከእብሪቱ ተመልሶ በግፍ ያሰራቸውን እነ እስክንድር ነጋን በአስቸኳይ ካልፈታና አገሪቷን ከቁማርና ከሸር በጸዳ መልክ ለማስተዳደር እስካልቆረጠና ነጻና ገለልተኛ ምርጫ እንዲካሄድ ካላደረገ በስተቀር ከስብሃት ነጋ የከፋ ውርደት ውስጥ በፍጥነት እንደሚገባ የሚያጠራጥር ነገር የለም።

እንደ እስክንድር ነጋ ያሉ ንፁሃን ሰዎች እንዴት እንደ ስብሃት ነጋ ካሉ የትህነግ ወንጀለኞችና ደም አፍሳሾች ጋር አብረው ይታሰራሉ? ንጹሃንና ወንጀለኞችን ሁለቱንም ወህኒ ቤት ማስገባት የተጨናበረውና የተወናበደው የአብይ አህመድ ፍልስፍና “መደመር” ይሆን እንዴ? ስብሃት ነጋና መሰሎቹ ለሰሩት ግፍና ወንጀል እስር ቤት መግባታቸውና ፍርዳቸውን መቀበላቸው ተገቢ ሲሆን እስክንድር ነጋና ባልደረቦቹ ምን አደረጉ? አብይ አህመድ እኮ የጊዜ ጉዳይ ሆኖ እንጅ ለስብሃት ነጋ በተላላኪነት ሲያገለግል በነበረበት ጊዜ እስክንድር ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነትና ዲሞክራሲ በመታገሉ ምክንያት በትህነግ በግፍ ታስሮ ዋጋ ይከፍል እንደነበር አይዘነጋም።

እስክንድር ነጋ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቅ ግፊት ለማድረግ እባክዎን ገለልተኛና ፖለቲካዊ ያልሆነ ዓለም አቀፋዊ ዘመቻችንን ይደግፉ፣ ይሳተፉ። ይህንን ዓለም አቀፋዊ ዘመቻ የጀመርነው ቀን December 18, 2020 እንደሆነ ለታሪክና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይመዝገብ። በቅድሚያ ተከሽነው የተጻፉ ኢሜሎችን ለዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለመላክ፣ የሴኔትና የምክር ቤት ተወካዮች ለማነጋገር እንዲችሉ የኢሜል መልዕክት መላኪያ ዝርዝራችን ላይ ይመዝገቡ። በዚህም መሠረት freeeskindernega.org ይጎብኙ እንዲሁም በትዊተር ላይ @FreeEskinderN እና Instagram ላይ @freeeskindernega ይከተሉን።