የአብይ አህመድ የርቀት መነጽር መቀሌን ሲመለከት፣ ደምቢዶሎን ግን አይቃኝም


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የአብይ አህመድ አገዛዝ ስልጣንን ከህወሃት ከወረሰ ወዲህ እጅግ ዘግናኝ የሆኑና በዓለም አቀፍ ደረጃም ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ጭፍጨፋዎች በአማራ ህዝብና በኦርቶዶክስ ተወኅዶ እምነት ተከታዮች ላይ እየደረሱ ነው። ለነዚህ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አብይ አህመድ በአብዛኛውና ወንጀሉን በመካድ አንዳንዴም በማቃለል ደንታ ቢስነቱን ሲገልጽ ቆይቷል። የጉዳቱ ሰላባዎች ግን ለሚደርስባቸው የዘር ማጥፋት (ጀኖሳይድ) ተጠያቂው የአብይ አህመድ አገዛዝ እንደሆነ በማስረጃ አስደግፈው እያቀረቡ ነው።

ከአንድ ዓመት በላይ ደምቢዶሎ ውስጥ አማራ በመሆናቸው ምክንያት በጥላቻ ባበደ መንጋ ታፍነው ጭካ ውስጥ የደረሱበት ስለማይታወቁ ልጃገረዶች አብይ አህመድ ምንም የሚተነፍሰው ነገር የለም። የአማራ ደም ከውሻ ደም ያነሰ ዋጋ ስለሚሰጠው ነው እንጅ ይህ ወንጀል ብቻ አብይ አህመድ የህዝብን ሰላምና ደህነት ማስጠበቅ ስላልቻለ ከስልጣኑ እንዲወገድ ማድረግ የሚገባው ነበር። አሁን ደግሞ አማራ ላይ ማላገጫና መሳለቂያ የሆነው ነገር መቀሌ ውስጥ የሚገኘውን ደብረ ፅዮንን ያለበትን ጉድጓድ መመልከት የቻለ የአብይ አህመድ የርቀት መነፅር (drone) ደምቢዶሎ ላይ የታፈኑትን ልጃገረዶች መመልከት አለመቻሉ ነው። ምናልባት በአገራችን በተደጋጋሚ መብራት ሲለሚጠፋ ይሆን ወይስ ባትሪ አልቆ ነው ማየት ያልተቻለው? ይህንን እጅግ የሚያሳዝን ነገር አስመልክተው ቀሲስ አስተአአየ ጽጌ ያስተላለፉትን መልዕክት አቅርበንላችኋል።