በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወታደራዊ አታሼ የሆኑት ጄኔራል አሜሪካንን ጥገኝነት ጠየቁ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽ/ቤት ወታደራዊ አታሼ ሆነው ሲሰሩ የነበሩት ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ ከኃላፊነት ተነስተዋል።
ጀኔራሉ ከሐላፊነት እንደተነሱ በሀገር መከላከያ ሚኒስትር በኩል ደብዳቤ እንደደረሳቸው በአሜሪካ ጥገኝነት መጠየቃቸውም ታውቋል።ሜጀር ጄኔራሉ ፍስሀ ኪዳኔ በሐገር መከላከያ ሰራዊት የምዕራብ እዝ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።
የምዕራብ እዝ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት በሰሜን ጎንደር ጭልጋና መተማ አካባቢ ከሱር ኮንስትራክሽን ጋር በመተባበር የቅማንትና የአማራ ህዝቦችን ግጭቶች በበላይነት መርተዋል።
ሜጀር ጀኔራል ፍስሀ ኪዳኔ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ከመምራት በተጨማሪ በወቅቱ በቦታው የተሰማራውን የመከላከያ ሰራዊት ከተልዕኮው ውጭ በመስጠት ላስፈጸሙት የሰባዊ መብት ጥሰቶች በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል።
አሁንም ከተሰጣቸው ሐገራዊ ተልዕኮ በማፈንገጥ በተለያዩ አለም ሀገራት ከሚገኙ ኤምባሲዎች ጋር በሚስጢር በመገናኘት የወንጀለኛው ትህነግን ተልዕኮ ሲያስፈጽሙ መቆየታቸው ታውቃል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ሀገራት የኤምባሲ አመራር ሆነው በሃላፊነት የሚሰሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ሲሉ አንድ የውጭ ጉዳይ ሚነስትር ከፍተኛ ባለስልጣን ገልፀዋል።