የመከላከያ ሠራዊታችን አክሱምን አድዋንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጠረ።

ዛሬ ኅዳር 11 2013 የመከላከያ ሠራዊታችን አክሱምን አድዋንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጠረ።
በምዕራብ ግንባር የሕወሐት ጁንታን ኃይል እያጠቃ ያለው የመከላከያ ሠራዊታችን፣ ከሽሬ በኋላ ሰለህለሃ ላይ የመሸገ የሕወሐት ኃይል ገጥሞት ነበር። ሰለህለሃ ላይ የመሸገው የጁንታው ኃይል መንገዱን በዶዘር ቆርጦና አስፓልቱን አበላሽቶ በቦታው ከባድ መከላከል አድርጓል።
የመከላከያ ሠራዊቱ የጁንታውን ተከላካይ ኃይል ሠብሮ በመግባት አክሱምን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።
ከአክሱም ወደ አድዋ በነበረው ጉዞ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ የጁንታው ኃይል ለመከላከል ቢሞክርም፣ በመከላከያ ሠራዊቱ ድል ሆኗል።
መከላከያ እንቲጮንና የአዲግራትን ዙሪያ ተቆጣጥሮ ወደ አዲግራት ከተማ እየገሠገሠ ይገኛል።
አያሌ የጁንታው ተዋጊዎች እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከድተው ከጁንታው ጋር ሆነው ሲዋጉ የነበሩ ወታደሮችም ይገኙበታል።