መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን በቁጥጥሩ ስር እንዳዋለ ገልጿል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

መከላከያ ሰራዊት የሁመራ ኤርፖርትን በቁጥጥሩ ስር እንዳዋለ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የልዩ ኃይል አባላት ፣ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች እጃቸው እንደሰጡ ገልጿል።

ከላይ የተያያዙት ፎቶዎች ⬇️⬇️⬇️ የሁመራ ኤርፖርት አሁናዊ ገፅታን የሚያሳዩ ናቸው ብሎ ብሄራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ (ETV/EBC) አሰራጭቷቸዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ዘራፊው የህውሓት ቡድን ከጠላት ጋር ጥምረት በመፍጠር ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት የነበረውን የሁመራ ኤርፖርት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።በርካታ ህውሓት ያደራጃቸው የልዩ ኃይል፣ የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት እጃቸውን እየሰጡ ነው።
ሰራዊቱ ዘራፊው የህውሓት ቡድን ያደረሰበትን ድንገተኛ ጥቃት በመመከት የመልሶ ማጥቃት ስራ እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ከዳንሻ ጀምሮ በርካታ ቦታዎችን እየተቆጣጠረ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል።
⬇️⬇️⬇️ በሀገር መከላከያ ቁጥጥር ስር የዋለው የሁመራ ኤርፖርት አሁናዊ ገፅታ እና እጃቸውን የሰጡ የጽንፈኛው
                                                     ህወሓት ቡድን ልዩ ኃይል አባላት ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️