ፓትሪያርክ አቡነ መርቆሪዮስ የፊታችን ሳምንት አዲስ አበባ ሲገቡ እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ ለመቀበል ዝግጅት ተጀምሯል

ላለፉት 27 ዓመታት በስደት የቆዩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁህ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዮስ የፊታችን ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ ይጠበቃል።

ፓትሪያርኩ የአሜሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከሚመለሱት ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ ጋር አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት ዝግጅቱን በሰፊው ጀምሯል።

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አንድነት ሲጸልዩ የቆዩ በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፓትሪያርኩን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን በነቂስ ወጥተው ለመቀበል በጉጉት እየጠበቁ ናቸው። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን። ተከታተሉ።


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV ON YOUTUBE