መደመር መንገዳችን ብልጽግና መዳረሻች ግባችን ሆኖ ይቀጥላል -ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳረጋገጡት ኢትዮጵያ በመደመር ፍልስፍና ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ ትቀጥላለች፡፡

”የመደመር መንገዳችን ያለ ልዩነት ለሁሉም ዜጎቻችን የተዘረጋ አዲስ የብርሃን መንገድ ነው፡፡ መዳረሻ ግባችን ብልጽግና ነው”ም ብለዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያውያን ለሁለንተናዊ ዕድገት በጋራ እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
”ብልጽግና ንጋት እንጂ ሌት ሆኖ ማንንም አይጋርድም፣ አይሸፍንምም” በማለትም ዜጎች ለተሻለ ሕይወት እንዲተጉ አስገንዝበዋል፡፡
”በመደመር የማይጠገን ልዩነት፣ በብልጽግና የማይኮሰምን እርዛት፣ በሐቅ የማይረታ ሐሰት አለመኖሩን ዐውቀን በጽናት ጉዟችንን እንቀጥላለን” ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባለፈው ዓመት ”መደመር” በሚል ርዕስ መጽሐፋቸውን አሳትመዋል፡፡የኢትዮጵያውያን ሕይወት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከያዝነው ዓመት ጀምሮ የሚተገበር የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ በፕላንና ልማት ኮሚሽን በመዘጋጀት ላይ ነው፡፡