የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ ምክክር አደረጉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ የምክክር ያካሄዱ ሲሆን በመድረኩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ እና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩ ሀገራዊ መግባባት እንዲፈጠር መንግስት እና ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር አንድነትና ብሄራዊ መግባባት ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ችግሮች እየተፈጠረ መሆኑ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ችግሮችን ለመቅረፍ ከመፈራረጅ በመውጣት ለሀገር አንድነት ሊሰራ እንደሚገባ ተነስቷል።
ያለሰላም ምንም ማድረግ ስለማይቻል የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ መንግስት የህግ የበላይነትን ሊያስከብር ይገባልም ተብሏል።
በህብረተሰቡ ዘንድ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት መንግስት ከህዝብ ጋር ተቀራርቦ መነጋገር እንዳለበትም ተገልጿል።
መድረኩ ላይ የሀገሪቱ የፓለቲካ ሂደት የሚያመላክቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበዋል።