በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ህንፃ ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል፡- የባንኩ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ
በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ካሉት 3 የቢሮ ህንፃዎች በአንደኛው ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ፣ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የባንኩ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ አስታውቀዋል።
የእሳት አደጋውን በፍጥነት መቆጣጠር በመቻሉም በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ለኢቲቪ በስልክ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አረጋግጠዋል።